Saturday, February 4, 2012

የሰበር መዝገብ ቁጥር 34621 ጉዳት የመድን ሽፋንየሰ/መ/ቁ. 34621
ሐምሌ 30 ቀን 2001 ዓ.ም
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ
       ታፈሰ ይርጋ
       ፀጋዬ አስማማው
       አልማው ወሌ
       ዓሊ መሐመድ
አመልካች፡- ኒያላ ኢንሹራንስ አ/ማ - ጠበቃ አቶ በረከት በርሄ ቀረበዋል
ተጠሪ፡- አቶ ሐጐስ ገ/ድህን - ጠበቃ አቶ ገ/ሄር ተስፋይ ቀርበዋል
      ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ከመረመር በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል፡፡
ፍ ር ድ
      ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካች ታህሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው አቤቱታ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 41455 መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ግድፈት የተፈጸመበት ነው በማለት እንዲሻርለት ስለጠየቀ ነው፡፡
      ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች በስር ከሳሽነት፣የአሁኑ ተጠሪ እና ሌሎች በዚህ ሰበር ችሎት ተከራካሪ ያልሆኑ ሁለት ሰዎች ተከሳሾች በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ስር ከሳሹ (የአሁኑ አመልካች) መስከረም 14 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈ ያቀረበው ክስ አጭር ይዘቱ ደንበኛዬ ከጣሊያን ሃገር ገዝቶ ለሚያስገባቸው የጫማ ሶል መስሪያ ኬሚካሎች በጉዞ ላይ እንዳሉ ለሚደርስባቸው ጉዳት የመድን ሽፋን የሰጠሁ ሲሆን እነዚህ የመድን ሸፋን የሰጠኋቸውን ንብረቶች ከጅቡቲ ወደብ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለማጓጓዝ የተባበሩት የጭንት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር(1ኛ ተከሳሽ) ግዴታ በመግባት ተረክቦ በአቶ ሐጐስ ገ/መድህን(2ኛ ተከሳሽ) ንብረት በሆነችው እና በአቶ ፋሲል ሐጐስ(3ኛ ተከሳሽ) ንብረት በሆነችው እና ቁጥሯ 3-37484/3-04254 በሆነች መኪና ተጭኖ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ የመኪናው ተሳቢ በመገለበጡ ግምቱ ብር 129,333.93(አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ሰላሳ ሦስት ብር ከዘጠና ሦስት ሳንቲም) በሆነ 42 በርሜል እና 4 ጀሪካን ኬሚካል ላይ ጉዳት በመድረሱ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለደንበኛዬ መድህን ከፍያለሁ እና ተከሳሾቹ ይህንን የገንዘብ መጠን ከነወለዱ ይክፈሉኝ የሚል ነው፡፡

      ተከሳሾቹም ለቀረበባቸው ክስ መልስ እንዲሰጡ በታዘዘው መሰረት፣
1ኛ ተከሳሽ በሰጠው መልስ ከሳሹና ደንበኛዬ የሚለው ባለንብረት የፈጸሙት የኢንሹራንስ ውል ተገቢውን የአፃፃፍ ፎርም ያላሟላ በመሆኑ ለከሳሹ የመዳረግ መብት አይፈጥርለትም፤ለከሳሹም የመደረግ መብት በባለንብረቱ አልተሰጠውም፤እንዲሁም ክሱ በይርጋ ይታገዳል፤በኢንሹራንስ ውሉ የተዋዋይ ወገኖችና የምስክሮች ፊርማ የሌለ በመሆኑ ውጤት የለውም ብሏል፤
 2ኛ. ተከሳሽ ደግሞ እኔ የማጓጓዙ ውል ተዋዋይ አይደለሁም፤እቃው የተጫነበት ንብረት የእኔ ሳለመሆኑም የሚያስረዳ ማስረጃ አልቀረበም፤አደጋው በደረሰ በ7 ቀናት ውስጥም ያልቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብሏል፤
  3ኛ. ተከሳሽም የተባለው እቃ እልጫነኩም፤ክሱም በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት መልሷል፡፡
      የስር ፍርድ ቤቱም በግራ ቀኙ ወገኖች መካከል የቃል ክርክር ካካሄደ በኋላ ከላይ ላቀረቡት ክርክሮች እንደሚከተለው ወስኗል፣ይኸውም የስር ከሳሽ የመዳረግ መብት አለኝ በማለት ክሱን ያቀረበው ወይም መብቱ መነጨ የሚለው ኢንሹራንሱን ከከፈለው ደንበኛው ጋር ካደረገው የኢንሹራንስ ውልና ይህ ደንበኛው በሱ መብት ተደርጐ ክሱን በተከሳሾቹ ላይ ማቅረብ እንደሚችል ከፃፈለት ደብዳቤ በመሆኑና ተደረገ የተባለው የኢንሹራንስ ውል በሚመለከት በንግድ ሕግ አስገዳጅ የሆነ የተለየ ፎርማሊቲ ያልተቀመጠለት በመሆኑ የኢንሹራንሱ ውል የፎርማሊቲ ጉዳይ የሚታየው በፍታብሄር ሕጉ በተቀመጠው በጠቅላላ ውል ዓንቀፆች 1725፣1727 እና 1720(1) መሰረት ተደርጐ በመሆኑና ከሳሹ ከደንበኛው ጋር ያደረገው የኢንሹራንስ ውል በግራ ቀኙ ወገኖችና በምስክሮች ያልተፈረመ በመሆኑ ህጋዊ እውቅና የለውም፣አይጸናም፤ ስለሆነም የከሳሹ ደንበኛ በሌለ የኢንሹራንስ ውል ተመስርቶ ለከሳሽ የፃፈለት የመደረግ መብት ህጋዊ ውጤት የለውም፣ 2ኛው ተከሳሽም የንብረቶቹ አጓዥ ተብለው በማጓጓዝ ሰነድ እስካልተጠቀሱ ድረስ የመኪናው ባለቤት በመሆናቸው ብቻ አጓዥ ሊባሉ ስለማይገባ በውልም ሆነ ከውል ውጭ መሰረት ያደረገ ክስ ሊቀርብባቸው አይገባም የሚል ነው፡፡
      ከላይ የሰፈረውን የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በመቃወም የአሁኑ አመልካች ወደ ፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ወገኖች ካከራከረ በኋላ በኮ/መ/ቁ. 41455፣መስከረም 23 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ጉዳዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቶታል፡፡
      በስር ፍ/ቤቶቹ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት አመልካቹ ታህሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችሎት ያቀረበ ሲሆን፣አጭር ይዘቱም፣ከደንበኛዬ ጋር ህጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል በማድግ እቃዎቹ በተጠሪው መኪና ከወደብ ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ እያለ አደጋ በመድረሱ ለደንበኛዬ በክስ የቀረበውን ገንዘብ መክፈሌ ተረጋግጦ እያለ፣የመኪናዋ ባለቤት ተጠሪው መሆናቸው እና የጭነት ውሉ የተደረገው ከወኪላቸው (የስር 1ኛ ተከሳሽ) ጋር በመሆኑ በንግድ ህጉ መሰረት የእቃው አጓዥ መባል ሲገባቸው አጓዥ መሆናቸው በሰነዱ አልተጠቀሱም፣ስለሆነም አጓዥ አይባልም፤የመኪናዋ ባለቤት ቢሆንም ጉዳዩ የተያያዘው ከውል ጋር በመሆኑ ከውል ውጭ መሰረት በማድረግ ሊጠየቁ አይገባም በማለት የተሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊሻረልኝ ይገባል የሚል ነው፡፡
      ተጠሪውም ነሐሴ 07 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው በስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረው ማህበር የእኔ ወኪል አይደለም፤ እኔ የፈጸምኩት የእቃ አጓዥነት ውል የለም፤አመልካች ገንዘቡ ከስር 3ኛ ተከሳሽ እንዲያገኝ ተፈርዶለት እያለ አላግባብ በእኔ ላይ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
      ይህ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር ከላይ እየተገለፀ በመጣው መልኩ ከተገነዘበ በኋላ፣
1.   አመልካች ከደንበኛው ጋር የፈጸመው ህጋዊ የኢንሹራንስ ውል አለ ወይስ የለም?
2.   አመልካች ለደንበኛው ተክቶ ወይም ተደርጐ በስር ተከሳሾች (በእነ ተጠሪ) ክስ ሊመሰረት ይችላል ወይስ አይችልም?
3.   ተጠሪው የእቃው ማጓዝ ውል ወስደዋል ወይስ አልወሰዱም? በሌላ አባባል ተጠሪው በዚህ ጉዳይ አጓዥ ናቸው ወይስ አይደሉም?
     የሚሉ መሰረታዊ ጭብጦችን በማውጣት ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምሮታል፡-
      የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ የስር ፍርድ ቤቶቹ የሰጡት ትርጉም በተጠሪውና በደንበኛው መካከል በሕግ የሚጸና የኢንሹራንስ ውል የለም የሚል ለዚህም የሰጡት ምክንያት በውሉ ላይ ተዋዋይ ወገኖቹና ምስክሮች ስላልፈርሙበት በሕግ የሚፈለግበትን ተገቢ ፎርማሊቲ አላሟላም፤የንግድ ሕጉ የኢንሹራንስ ውል ይዘት ከሚዘረዝር በስተቀር ስለውሉ ፎርማሊቲ የሚለው ነገር ስለሌለ የኢንሹራንስ ውል ፎርማሊቲ በሚመለከት በፍትሃብሄር ሕግ ውስጥ በጠቅላላ ውሉ ዓንቀጽ 1725 እና 1727 በተመለከተው መሰረት መከናወን እንዳለበት ማለትም ውሉ የግድ በጽሁፍ መዘጋጀት ያለትና ተዋዋይ ወገኖችና ምስክሮች የግድ ሊርፈርሙት እንደሚገባ፣ይህ ሳይሟላ ከቀረ ግን በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር ዓንቀጽ 1720(1) መሰረት ውሉ እንደረቂቅ የሚቆጠርና ምንም አይነት ውጤት የማያስከትል ነው፤በመሆኑም አመልካች ከደንኛ ጋር ያደረገው የኢንሹራንስ ውል በተከሳሾቹ ላይ ግዴታ ሊያስከትል አይችልም የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ የንግድ ሕጉ ስለ የኢንሹራንስ ውል ፎርማሊቲ ምንም ነገር አላለም የተባለው ተገቢነት የለውም፡፡ ምክንያቱም የንግድ ሕግ አንቀጽ 657 ስለ ውሉ ፎርማሊት የሚደነግግ ሣሳብ አስፍሯል፤ ይኸውም የኢንሹራንስ ውል በኢንሹራንስ ውል ፖሊሲ በሚባል ጽሁፍ እንደሚደገፍና የመድህን ገቢው ጥያቄ መሰረት በማድረግ በፖሊሲው ላይ መድህን ሰጭው ከፈረመ ህጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት በመድህን ሰጭው እና በመድህን ገቢው መካከል እንደሚመሰረት ነው፤ይህ ሁኔታ ደግሞ የንግድ ሕጉ ልዩ የሆነ የኢንሹራንስ ውል አፈፃፀም የሰፈረ እንጂ ጉዳዩ በጠቅላላ የውል ሕግ የሚመራ ግንኙነት አይደለም፤ይህ ሰበር ችሎትም የኢንሹራንስ ውል አለ ለማለት ተመሳሳይ ትርጉም በሰ/መ/ቁ. 24703 ሚያዝያ 09 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡ ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶቹ በአመልካችና በደንበኛው መካከል የተደረገው ውል ሁለቱ ወገኖች እና ምስክሮች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1725 እና 1727 በሚያዙት መሰረት ባለመፈረማቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1720/1/ መሰረት የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት የለም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ ሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡ በመሆኑም በአመልካችና በደንበኛው መካከል ህጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት አለ ብለናል፡፡
      ሁለተኛው ጭብጥ  በተመለከተ የአመልካች ደንበኛ ሐምሌ 17 ቀን 1995 ዓ.ም የተፃፈ ሰነድ አዘጋጅቶ አመልካቹ በእርሱ እግር ተተክቶ መብቱን የማስከበር ወይም የመደረግ መብት እንዳለው ቢያረጋግጥም፣የስር ፍ/ቤቶቹ በሰጡት ፍርድ ይህ የመደረግ መብት ሕጋዊ ከሆነ የኢንሹራንስ ውል የመነጨ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአመልካችና በደንበኛው መካከል ሕጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት እንዳለ በላይኛው ጭብጥ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለሆነም አመልካቹ ን/ሕ/ቁ. 683 መሰረት በደንበኛው እግር ተደርጐ በተከሳሾቹ ላይ ክስ ማቅረብ የሚያስችለውን መብት ከደንበኛው አግኝቶ እያለ የስር ፍ/ቤቶቹ ሳይቀበሉት መቅረታቸው መሰረትዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ተገቢነት የለውም ብለናል፡፡
      ሦስተኛውን ጭብጥ በሚመለከት አመልካቹ ተጠሪው የመኪናዋ ባለንብረት በመሆናቸው አጓዥ ናቸው፤በስር ፍ/ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረው የተባበሩት የጭነት ማመላለሻ  ንብረቶች ማህበር ለተጠሪው ጥቅም ሲባል የሚጫን ነገር ከማፈላለግ ውጭ ጥቅሙ ለተጠሪው የሚውል በመሆኑ በን/ሕ/ቁ. 566/የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2251 መሰረት የትራንስፖርት ስራው በውክልና የሚያስተዳድር አካል ነው፤ስለሆነም ተጠሪው አጓዥ መባል አለበት ሲል ተጠሪው ደግሞ አጓዥ እንዳልሆኑ በመግለጽ የአመልካቹ አባባል የሚደግፍለት ማስረጃ አልቀረበም በማለት ይከራከራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳት ያደረሰችውን የአሁኑ ተጠሪ መኪና በሚመለከተ ከአመልካቹ ደንበኛ ጋር የአሁኑ ተጠሪ መኪና በሚመለከት ከአመልካቹ ደንበኛ ጋር የመጓጓዣ ውል በቀጥታ የፈጸመው በስር ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የነበረው (የተባበሩት የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር) ቢሆንም ይህ አካል ያደረገው ውል ተጠሪውን በመወከል ነው፤ምክንያቱም የዚህ አካል የስራ ድርሻ በማህበሩ የታቀፉት መኪኖች የጭነት ስራ እንዲያገኙ ከማድረግ አልፎ የእያንዳንዱ መኪና የጭነት ኪራይ ባለቤቱ ነው፣በአሁኑ ክርክርም ተጠሪው መኪናቸው በተባበሩት የጭነት ማመላለሻ ማህበር ከመታቀፏ ውጭ የመኪናው ገቢ በቀጥታ ተጠቃሚ ናቸው፤ስለሆነም በንግድ ሕ/ቁ. 566 እና የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2251 መሰረት ተጠሪው ከአመልካቹ ደንበኛ ጋር የጭነት ማጓዝ ውል የነበራቸው ሆነው እያለ የስር ፍ/ቤቶቹ ተጠሪው አጓዥ አይደሉም በማለት የደረሱበት ድምዳሜ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡
ው ሳ ኔ
1.   የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 43650፣ሰኔ 16 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 41455፣መስከረም 23/2000 ዓ.ም የሰጧቸው ፍርዶች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል፡፡ ይፃፍ፡፡
2.   ተጠሪው ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ብር 129,333.93(አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ሰላሳ ሦስት ብር ከዘጠና ሦስት ሣንቲም) እንዲሁም ክሱ ከቀረበበት ከመስከረም 14/1997 ዓ.ም ጀምሮ 9% ወለድ ተከፍሎ እስኪያልቅ ለአመልካች እንዲከፍለው ተወስኗል፡፡
3.   ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ ብለናል፡፡
       ጉዳዩ ያለቀ በመሆኑ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
                              የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ቤ/ኃ
             
የሰበር መዝገብ ቁጥር
የሰ/መ/ቁ. 34621

No comments:

Post a Comment