Saturday, February 4, 2012

የሰበር መ.ቁ. 3779 የመድን ሽፋን የማጓጓዝ ውል

የሰ/መ/ቁ. 37799
ሐምሌ 29 ቀን 2001 ዓ.ም
ዳኞች፡-  መንበረፀሐይ ታደሰ
        ዓብዱልቃድር መሐመድ
        ሒሩት መለሰ
        ታፈሰ ይርጋ
        ሱልጣን አባተማም
አመልካች፡- የባህርና ትራንዚት አግልግሎት ድርጅት - ነ/ፈጅ በዛብህ አመዴ ቀረቡ
ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ሰናይት በዳሣ
ፍ ር ድ
      ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ተጠሪ በፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የመሰረተው ክስ ነው፡፡ ተጠሪ ባቀረበው ክስ ደንበኛው የሆነው አዋሽ ወይን ጠጅ አ/ማ ለፋበሪካው አገልግሎት የሚውል የጠርሙስ ማጠቢያ ማሽን በጉዞ ላይ ለሚደርስበት ጉዳትና ውድመት የመድን ሽፋን ሰጥቷል፡፡ የተጠሪ ደንበኛ የጉምሩክ አስተላለፊነት ውክልና ቀጥሎም የማጓጓዝ ትእዛዝ ለአመልካች የሰጠ ሲሆን ማሽኑን በስር 2ኛ ተከሣሽ በነበሩት ግለሰብ መኪና አስጭኖ ሲያመጣ ተሽከርካሪው ተገልብጦ በማሽኑ ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ማሺኑም ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ ብር 2,200,856.43 ለደንበኛው ስለከፈለ አመልካች በገባው የውክልናና የማጓጓዝ ውል መሰረት፣በንግድ ሕግ ቁጥር 590 ባለበት ሃላፊነት፣2ኛ ተከሣሽም የተሽከርካሪው ባለንብረት በመሆናቸው ሁለቱም ገንዘቡን ሊተኩ ይገባል በማለት ጠይቋል፡፡ ፍ/ቤቱም ክርክሩን ተመልክቶ አመልካች እቃውን ያጓጓዘው በውክልና ስልጣን በመሆኑ ሊጠየቅ አይገባም በማለት 2ኛው ተከሣሽ ብቻ ገንዘቡን እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡

      ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ አመልካች እቃውን ያጓጓዘው ራሱን ችሎ እንጂ በውክልና ስላልሆነ ለጉዳቱ ኃላፊ ሊሆን ይገባል በማለት ከስር 2ኛ ተከሣሽ ጋር ክስ የቀረበበትን ገንዘብ በአንድነትና በነጠላ እንዲከፍል ወስኗል፡፡
      የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው፡፡ ይህ የሰበር ችሎትም አመልካች ማሽኑን ያጓጓዘው በውክልና ነው ወይስ እራሱን ችሎ ነው የሚለውን ነጥብ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ አድርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ግራ ቀኙ ቀርበው ክርክራቸውን በቃል አሰምተዋል፡፡ ችሎቱም አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካላቸው የሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ ተመክቷል፡፡
      ከፍ ሲል እንደተገለጸው የተጠሪ ደንበኛ ያስመጣውን የጠርሙስ ማጠቢያ ማሽን አመልካች ያጓጓዘው መሆኑ አከራካሪ አልሆነም፡፡ አከራካሪው የሆነው ነጥብ አመልካች ማሽኑን ያጓጓው እራሱ አጓጓዥ ሆኖ ነው ወይስ በውክልና ነው የሚለው ነው፡፡
      አመልካች እቃ አስተላላፊ ለመሆኑ ተጠሪም በክሱ ገልፆታል፡፡ እቃ አስተላላፊ ምን ማለት እንደሆነ እና ምን ምን ስራዎችን እንሚሰራ ስለእቃ አስተላላፊነት እና የመርከብ ውክልና ስራ ፈቃድ አስመልክቶ የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 37/90 ያመለክታል፡፡ በዚሁ በተጠቀሰው ደንብ አንቀጽ 2/1/ ስር እቃ አስተላላፊ በአገር ውስጥ ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ እቃ ተቀባይነት ወይም እቃ ላኪን በመወከል የጉምሩክ፣የመደብ ወይም ሌሎች ስርአቶች አስፈጽሞ ገቢ ወይም የወጪ እቃዎችን ወደብ እንዲገቡ ወይም እንዲወጡ የሚያደርግ ሲሆን እቃን የማጓጓዝና የማስረከብን ስራም ይጨምራል፡፡ ይህ ድንጋጌ በጥቅሉ ሲታይ እቃ አስተላለፊው ስራውን የሚያከናውነው እቃ ላኪዎችን ወይም ተቀባዮችን በመወከል በውክልና ስልጣን መሆኑን የሚያሣይ ነው፡፡ በእርግጥ የእቃ ማጓጓዝ ተግባሩን እንዴት ሊያከናውን እንደሚችል በደንቡ አንቀጽ 3/6/ እና /7/ ስር ተለይቶ ተቀምጧል፡፡ በአንቀጽ 3/6/ ስር እቃ አስተላላፊው የራሱ የትራንስፖርት አግልግሎት ካለው የእቃ ማጓጓዙን ተግባር የሚያከናውነው እንደ አጓጓዥ ሆኖ እንጂ በውክልና ስልጣን አለመሆኑ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ይህም በአንቀጽ 2/1/ ስር የተመለከተው የውክልና ስልጣን ልዩ ሁኔታ(exception) ነው፡፡
      በሌላ በኩል ግን የራሱ ትራንስፖርት ከሌው ወይም ባለእቃው የራሱን ማጓጓዣ ካላቀረበ እቃ አስተላለፊው ማጓጓዣ ተከራይቶ  እቃውን እንደሚያጓጉዝ በንኡስ አንቀጽ 7 ስር ተመልክቷል፡፡ ይህ ድንጋጌ በንኡስ አንቀጽ 6 ስር በግልጽ እንደተመለከተው የማጓጓዝ ስራውን እንደ አጓጓዥ ሆኖ እንደሚሰራ አያስቀምጥም፡፡ ከፍ ሲል እንደተገለጸው ደግሞ እቃ አስተላላፊ ስራውን ሁሉ የሚያከናውነው በውክልና በመሆኑ በእራሱ ስም ስለራሱ ሆኖ ይሰራል ተብሎ በንኡስ ቁጥር 7 ስር ልዩ ሁኔታ (exception) ስላልተመለከተ የማጓጓዝ ተግባሩን የሚያከናውነው በውከልና መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
      በሌላ በኩል የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች የማጓጓዝ ውሉን በራሱ ስም መፈጸሙ የማጓጓዝ ተግባሩን የፈፀመው እንደ አጓዥ ሆኖ ነው በማለት ወስኗል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው ግን እቃ አስተላላፊው እቃውን በወደብ ማስተላለፍ፣የወደብና የጉምሩክ ስርአቶችንና የእቃ ማጓጓዝ ተግባርን በሙሉ የሚፈጽመው በውክልና ነው፡፡ እንደ አጓዠ ሆኖ የሚቆጠረው የማጓጓዙን ስራ በራሱ ማጓጓዣ ካጓጓዘ ብቻ ነው፡፡ የማጓጓዣ ውሉን በስሙ መፈረሙ ብቻ ስራው በውክልና ያልተሰራ መሆኑን አያመለክትም በእርግጥ በፍ/ሕ/ቁ. 2251 የተገለጸው የእቃ አስተላለፊ በደንብ ቁጥር 37/90 ስር ከተመለከተው ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሣሣይ ተግባር የሚፈጽም ባይሆንም እቃ አስተላለፊው ስራውን የሚያከናውነው በራሱ ስም ሆኖ ለወካዩ ጥቅም መሆኑን ያመለክታል፡፡ ስለሆነም የእቃ አስተላላፊ በራሱ ስም የሚያደርጋቸው ተግባሮች ለወካዩ ጥቅም በውክልና ስልጣን የሚፈጸሙ ናቸው ማለት ነው፡፡
      አመልካች ውክልና ነው ከተባለ ተጠያቂ ሊሆን የሚችለው የውክልና ስራው በክፍት ያደረገ መሆኑ ከተረጋገጠ ብቻ እንጂ ጉዳት ስለደረሰ ብቻ በኃላፊነት ተጠያቄ እንደማይሆን በንግድ ሕግ ቁጥር 683/3/ ስር ተመልክቷል፡፡ በተያዘው ጉዳይ ደግሞ አመልካች  ስራውን በክፋት በማከናወኑ ጉዳት ያደረሰ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም፡፡ በመሆኑም አመልካች ለደረሰው ጉዳት በኃላፊነት የሚጠየቅበት የሕግ መሰረት የለም፡፡
      ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶችም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች ኃላፊ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት፡፡
ው ሳ ኔ
1.  የፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 28225 በ7/08/2000 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል፡፡
2.  የፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 40949 በ5/3/99 የሰጠው ውሣኔ ጸንቷል፡፡
3.  አመልካች የማጓጓዝ ስራውን የሰራው በውክልና ስልጣን በመሆኑ ኃላፊነት የለበትም ብለናል፡፡
4.  ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ፡፡
               መዝገቡ ተዘግቷል ለመ/ቤት ይመለስ፡፡
                                   የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ቤ/ኃ

1 comment: