Thursday, March 5, 2020

ሰ/መ/ቁ. 36259 ሠራተኛ ማነው?


የሰ//. 36259
የካቲት 12 ቀን 2001 .
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ
ታፈሰ ይርጋ
ፀጋዬ አስማማው
አልማው ወሌ
ዓሊ መሐመድ
አመልካች፡- ሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝ /ፈጅ ግርማ ዘለቀ ቀረቡ
ተጠሪ፡- እነ አቶ አሰናቀ መንግስቱ - ወኪሎቻቸው ቀረቡ
 መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
 ዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪዎች የካቲት 28 ቀን 1998 . በተፃፈ የክስ ማመልከቻ በአሁኑ አመልካች ድርጅት የተቀጠሩበትን ጊዜ፣ የተቀጠሩበት የስራ መደብ በምርት ክፍል ውስጥ በጫኝና አውራጅነት መሆኑን፣የደመወዝ አከፋፈም ቀደም ሲል በየወሩ ብር 240.00 ይከፈላቸው እንደነበርና የከሣሾች የስራ ባልደረባ የነበሩት ግለሰቦች በድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ እንቀጠር በማለት የክስ አቤቱታ በማቅረባቸው ብቻ ተከሣሽ የከሣሾችን ላልተወሰነ ጊዜ የመቀጠር መብት ለመገደብ በማሰብ የስራ ባህርይውን ሣይለውጥ የአከፋፈን ሁኔታ ብቻ በመቀየር በኩንታል 0.35 ሂሣብ ብሎ በመተመን በየ15 ቀኑ በቁርጥ ክፍያ ሲፈጽምላቸው መቆየቱን ታህሳስ 23 ቀን 1998 . ደግሞ የስራ ውላቸውን ያላግባብ በማቋረጥ ሌሎች ሰራተኞችን መቅጠሩን በመዘርዘር ከስራ ከተሰናበቱበት ቀን ጀምሮ ያለው ደመወዝ ለእያንደንዳቸው ተከፍሎ ወደ ስራ እንዲመለስ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ 

የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ ይርጋንና የከሳሽ የመሆን መብትና ጥቅምን በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት በፍሬ ነገር ረገድ ደግሞ ከሳሾችን ተከሣሽ ድርጅት የማያውቃቸውና የስራ ውልና ግንኙነት የሌው መሆኑን እና ድርጅቱ አቶ ሄኖክ ሸዋ ከተባለ ግለሰብ ጋር ባደረገው የቁርጥ ክፍያ ከሣሾች ሲሰሩ የነበሩ መሆኑን እንዲሁም ሄኖክ ሸዋ የተባለ ከሣሽም በክርክሩ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ መሰረት መልስ እንዲሰጥና በስራ ላይ በደረሰው ዳትና ሌሎች አርባ አንድ ሰዎች በሚያነሱት የስራ መብት ጥያቄ ላይ ኃላፊነት እንዲወሰድና ተከሣሹ ድርጅት በነፃ እንዲሰናበት ዘንድ በመግለጽ ተከራክሯል፡፡ 
የስር /ቤትም ክሱን ከሰማና የግራ ቀኙን የጽሑፍ ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የከሣሾች ከስራ መሰናበት ባግባቡ ያለመሆኑን የሚያሣይ ጭብጥ በመያዝ የስራ ስንብቱ አግባብ አይደለም ወደሚለው ድምዳሜ ከደረሰ በኋላ አመልካች ድርጅት ከአቶ ሄኖክ ሸዋ ውጭ ያትን ከሣሾችን 6 ወር ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎ ወደ ስራ እንዲመልሣቸው ለሌሎች ሰራተኞች የሚደረገውን ጥቅማ ጥቅም እንዲያሟላላቸው እንዲሁም አቶ ሄኖክ ሸዋ የስራ መሪ ስለሆነ ስልጣን ባለው /ቤት ክስ የማቅረብ መብት እንዳላቸው በመግለጽ ወስኗል፡፡ 
የአሁኑ አመልካች በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፌደራል ከፍተኛ /ቤት አቅርቦ /ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር /ቤትን ውሣኔ በማጽናት እና ለተጠሪዎች ለእያንዳንዳቸው የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፍላቸው ወስኗል፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች /ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡
 የአመልካች ነገረ ፈጅ መጋቢት 03 ቀን 2000 . በፃፉት 5/አምስት/ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች /ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ ይዘቱም ባጭሩ በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የስራ ውል ግንኙነት የሌለ መሆኑን፣ተጠሪዎችን ቀጥሮ ያሰራቸው የነበረው ከአመልካች ድርጅት የቁርጥ ስራ ውል የተዋዋለው ሄኖክ ሸዋ የተባለው ግለሰብ መሆኑን፣የተጠሪዎች እና የአመልካች ግንኙነት የስራ ውል ላይ ያልተመሰረተ መሆኑን በበታች /ቤቶች የቀረቡት ማስረጃዎች የሚያረጋግጡት መሆኑንና የበታች /ቤቶች ውሣኔ አመልካችን ለዳት ወይም ለኪሣራ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ከመዋቅር ውጭ ትርፍ የሰው ሐይል እንዲይዝ ያለስራ ደመወዝ እንዲከፈል የሚያደርግ መሆኑን ዘርዝሮ ውሣኔ ሊሻር ይገባል በማለት መከራከሩን የሚያሣይ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ ሊታይ ይገባዋል በመባ ተጠሪዎች ቀርበው ከአመልካች ጋር የስራ ውል ግንኙነት ያላቸው መሆኑን፣አቶ ሄኖክ ሸዋ ከተባለ ግለሰብ ጋር ያደረት የቁርጥ ክፍያ ስምምነት አለመኖሩን፣ለተጠሪዎች የደመወዝ አከፋፈ መቀየሩም የአመልካች ሰራተኞች አይደም ሊያሰኝ የማይችል መሆኑንና የአመልካች የሰበር አቤቱታ እውነትነት የሌለው መሆኑን ግንቦት 06 ቀን 2000 . በፃፉት ማመልከቻ በመዘርዘር የበታች /ቤቶች ውሣኔ ሊፀና ይግባል በማለት ተከራክረዋል፡፡ የአመልካች /ፈጅም ግንቦት 30 ቀን 2000 . በፃፉት የመልስ መልስ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን አጠናክረው ተከራክረዋል፡፡
 የጉዳዩ  አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን የጽሑፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡ እንደመረመረውም በአመልካችና በተጠዎች መካከል የቅጥር ውል አለ ወይስ የለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ሊመረመር የሚገባው ሲሆን ሌሎች ነጥቦች በዚሁ ነጥብ ሊካተቱ የሚች ሆኖ አግኝቷል፡፡
 ከመዝገቡ የክርክር ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች በአመልካች ድርጅት የሲሚንቶ ጭነት ማውረድና መጫን ሲሰሩ የነበሩ መሆኑን፣ተጠሪዎች የቋሚ እንሁን ጥያቄ በአሰሪና ሰራተኛ ዳይ ወሣኝ ቦርድ አቅርበው ጥያቄቸው የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ  ቦርዱ ክሣቸውን ውድቅ ማድረን፣ተጠሪዎች ቀደም ሲል ይከፈላቸው የነበረው የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ በቁርጥ ሁኖ በየአስራ አምስት ቀኑ መሆኑን የቁርጥ ክፍያውን ከአመልካች ድርጅት ይቀበል የነበረው ሄኖክ ሸዋ የተባለ ሁኖ በተጠሪዎች ተወካይነት ስለመሆኑ እንዲሁም አቶ ሄኖክ ሸዋ ከአመልካች ድርጅት ጋር በሚያዝያ ወር 1996 . የፒስ ሬት የስራ ውል መዋዋላቸው የተረጋገጡ ዳዮች መሆናቸውን ነው፡፡ ሆኖም ተጠሪዎች በአመልካች ድርጅት ለረዥም ጊዜያት ተቆጥረው የቆዩ፣አቶ ሄኖክ ሸዋ ጋርም ምንም ዓይነት የስራ ውል ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል፡፡ በመሆኑም የአመልካችንና የተጠሪዎችን ክርክር አግባብነት ለመገንዘብ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ስር ሰራተኛ ማንነው? የስራ ውልስ እንዴት ይመሰረታል? የሚትን ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችትን ድንጋጌዎች መመልከት ተገቢነት ያለው ነው፡፡
 በአሰሪና ሰራተኛ ዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 2/3/ መሰረትሰራተኛበሚለው ትርም ለመሸፈን በአዋጁ አንቀጽ 4/1/ እንደተመለከተው ደመወዝ እየተከፈለው በአሰሪው መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ስራ ለአሰሪው ለመስራት በመስማማት ከአሰሪው ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙት ሊኖረው ይገባል፡፡ በመሆኑም የስራ ውል አንድ ሰራተኛ በአሰሪው መሪነት የአሰሪውን ስራ፣በወ ላይ ለተመለከተው የስራ ጊዜ ለመስራት የሚያቋቁመው ስምምነት ስለመሆኑ አዋጁ አንጽ 4/1/ ትርጓሜ ሰጥቶበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተጠቃሹ አንቀጽ ንኡስ ቁጥር 2 እና 3 ድንጋጌዎች የስራ ውል ተዋዋይ ወገኖች በው መሰረት የሚኖራቸውን መብትና ግዴታ በማያጠራጥር አኳኋን በሚያውቁበት ሁኔታ በግልጽ ማስፈር ያለበት ሲሆን ውም የስራውን ዓይነትና ቦታ፣ለስራው የሚከፈለውን ደመወዝ መጠን፣የስሌቱን ዘዴ፣የአከፋፈን ሁኔታና ጊዜ እንዲሁም ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ መያዝ እንደሚኖርበት አስቀምጧዋል፡፡ የስራ ውል በዚህ አኳኋን መደረግ የሚኖርበት ቢሆንም በህግ በተለየ አኳኋን ካልተደነገገ በቀር የተለየ ፎርም የማያስፈልገው፣ በማናቸውም ዓይነት ዘዴ ሊቋቋም የሚችል ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 5 ድንጋጌ መንፈስ ያስረዳል፡፡
 ወደተያዘው ዳይ ስንመለስም በስር ክርክሩም ሆነ በዚህ ሰበር ችሎት ግራ ቀኙ ካደረት ክርክር የተረጋገጠው ዳይ ተጠሪዎች ለአመልካች የልበት ስራ ሲሰሩ ቆይተው አቶ ሄኖክ የተባለ ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት ጋር በተዋዋለው የፒስ ሬት ስራ ተጠሪዎችን እየተቆጣጠሩ የሚያሰራቸው የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታም በሚሰራው የኩንታል ብዛት ሆኖ ተጠሪዎች የሚያገኙት በአቶ ሄኖክ ሸዋ በኩል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ እንዲህ ከሆነ ተጠሪዎች ከአመልካች ድርጅት ጋር በህ መሰረትሰራተኛበሚለው ትርም መሰረት የአሰሪና ሰራተኛ የውል ግንኙነት እንዳላቸው ያለመረጋገጡን መረዳት ይቻላል፡፡ በመሆኑም የስር /ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን ክርክር መርምሮ ተገቢውን ውሣኔ መስጠት ሲገባው በደፈናው በማለት የስራ የተቋረጠው ያላግባብ ወደሚለው ድምዳሜ መድረሱም ሆነ ተጠሪዎች 6 ወር ደመወዝ ተከፍሏቸው ወደ ስራ እንዲመለስ መወሰኑ እና የፌደራል ከፍተኛ /ቤትም በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የስራ ውል ግንኙነት መኖሩን ተጠሪዎች ባላረጋገጡበት ሁኔታ የስር /ቤትን ውሣኔ በማጽናት ለተጠሪዎች የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈልና ወደ ስራ እንዲመለሱ መወሰኑ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 2/3/ እና 4 ድንጋጌዎችን መንፈስ ባላገናዘበ ሁኔታ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል፡፡ በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል፡፡
1.             በፌዴራል ///ቤት በመ/. 21937 ሰኔ 26 ቀን 1999 . ተሰጠቶ በፌዴራል ከፍተኛ /ቤት በመ/. 57656 የካቲት 26 ቀን 2000 . የፀናው ውሣኔ በፍ/////. 348/1/ መሰረት በሙ ተሽሯል፡፡
2.            ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ከአመልካች ጋር የአሰሪና ሰራተኛ በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ውል ግንኙነት የላቸውም ብለናል፡፡
3.             ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻ ብለናል፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ /ቤት ይመለስ፡፡
                                    የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
/    

No comments:

Post a Comment