የሰበር መ/ቁ. 36848
ጥቅምት 11 ቀን
2ዐዐ1 ዓ.ም
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ
ሐጎስ ወልዱ
ሒሩት መለሠ
ተሻገር ገ/ሥላሴ
ሡልጣን አባተማም
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤ/ኃይል ኮርፖሬሽን
ተጠሪዎች፡- 1. መኰንን ግርማይ ቀረቡ፡፡
2. በዶ ዘለቀ ቀረበ
3. ፈጠነ አያዩ አልቀረበም
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍ ር ድ
በበኩላችንም አመልካች መጋቢት 26 ቀን
2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል፡፡ አቤቱታው በሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው ተጠሪዎች የአመልካች ሠራተኞች ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ነጥብ ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕ ጋር አገናዝበን መርምረናል፡፡
እንደምንመለከተው አከራካሪው ነጥብ በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል የስራ ውልን መሠረት የደረገ ግንኙነት ነበር ወይስ አልነበረም የሚለው ነው፡፡ ከስር ጀምሮ ከቀረበው የአመልካች ክርክር እንደሚታየው ተጠሪዎች በተባለው የምሰሶ ድጓድ ቁፋሮ ወይም የኤሌክትሪክ መስመር መዘርጋት ስራ አልተሣተፉም አይልም፡፡ ክርክሩ ይህን ስራ የሰሩት ከኔ ጋር የስራ ውል አድርገው ሣይሆን፣ ስራውን እንዲሠራ ኮንትራት ከተሰጠው ግለሰብ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ነው የሚል ነው፡፡ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ይህን ጭብጥ በመያዝ ማስረጃ እንደሰማና በዚህም አመልካች ስራውን በኮንትራት የሰጠው ግዛው ወንዳፍራሽ ለተባለ ሰው እንደሆነ፣ ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር የቅጥር ግንኙነት እንደሌላቸው፣ ግዛው ወንዳፍራሽ ክፍያውን ሲፈጽም እንደቆየ ማረጋገጡን በአንድ በኩል ሲገልጽ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተከሣሽ /አመልካች/ ከሱ ጋር የቀን ስራ ሲሰሩ አለመቆየታቸውን ሙ በሙ አልካደም፣ ክፍያው ሲፈፀም የነበረው ከአመለካቹ በተገኘ ገንዘብ ነው የሚትን ምክንያቶች በመስጠት አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ እንደሰጠ ለመገንዘብ ችለናል፡፡
በበኩላችን እንደምናየው አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የተደረገ የሥራ ውል እንደሌለ በግለጽ በማመልከት ተከራክሮአል፡፡ ተጠሪዎች የተባለውን ስራ ሊሠሩ የቻበትን ምክንያትም ከመግለፁም በላይ፣ በቆጠረው ማስረጃም እንደክርክሩ ጭብጥ አስረድቶአል፡፡ የሥር ፍ/ቤቶች ይህንኑ ሁኔታ በውሣኔዎቻቸው ላይ በሚገባ አስፍረው ግንዛቤ አግኝተው ሣለ ተቃራኒ የሆነውን ውሣኔ መስጠታቸው ትክክል አይደለም፡፡ ማንኛውም ክርክር ሊወሰን የሚገባው በቀረበው ክርክር ማስረጃ እና በሕ መሠረት ብቻ ነው፡፡ እነዚህን መሠረታዊ ቁምነገሮች በማለፍ የሚሰጥ ውሣኔ በማንኛውም መለኪያ ሕጋዊ ሊሆን አይችልም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔም ከቀረበው ክርክር፣ከተሰማው ማስረጃ እና ከሕ ውጭ የተሰጠ በመሆኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል፡፡
ው ሣ ኔ
1.
|
አቤቱታ የቀረበበት በአዳማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ6165 መጋቢት 14 ቀን 99 ዓ.ም ተሰጥቶ የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. ዐ52ዐዐ መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐዐ ያፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሠረት ተሽሮአል፡፡
|
2.
|
በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል የስራ ውል ግንኙነት ስለሌለ ተጠሪዎች በአመልካች ላይ የመሠረቱት የስራ ክርክርን የሚመለከተው ክስ የሕግ መሠረት የለውም በማለት ወስነናል፡፡ ወጪና ኪሣራ ይቻቻ፡፡
|
መዝገቡ
ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ተ.ወ
No comments:
Post a Comment