Saturday, March 7, 2020

የሠ/መ/ቁ 38543 ፕሮፊደንት ፈንድ


የሠ//38543
ግንቦት 18 ቀን 2001

1. ዓብዱልቃድር መሐመድ
  2. ሐጎስ ወልዱ
  3. ሂሩት መለሠ
  4. በላቸው አንሺሶ
  5. ሱልጣን አባተማም

አመልካች፡- /ር ታደሰ ይርጋ - ቀረበ
ተጠሪ፡- የቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ጠበቃ ክፍሌ ቀረበ

 መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል
ፍ ር ድ
 ዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የሥር ከሣሽ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በመሠረቱት ክስ በተጠሪ ድርጅት (/ቤት) በሰውነት ማጐልመሻ መምህርነት ስሠራ ቆይቻለው፡፡ ተጠሪ ጥቅምት 25/99 .ም በተፃፈ ደብዳቤ ያለጥፋቴ ከስራ አሰናብቶኛል፡፡

 ስለዚህ የሥራ ውሌ ከህግ ውጭ የተቋረጠ ስለሆነ ውዝፍ ደሞዜ ተከፍሎኝ ወደ ስራ እንዲመልሰኝ ሲ ጠይቋል፡፡ ተጠሪም ለፍ/ቤቱ በሰጠው መልስ አመልካች ከሥራቸው የተሰናበቱት ካባቸው የባህሪ ችግር በአስተዳደሩ ሥራ ጣልቃ በመግባት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ችግር በመፍጠራቸው በአስተዳደር ላይ ቅስቀሳ በማድረግ በሥራ ሰዓት ሰራተኛውን ስብሰባ በመጥራት ጥበቃ መጠጥ ጠጥቶ እንዲገባ በማድረጋቸው እና የተለጠፈ ማስታወቂያ በመገንጠላቸው ነው የተሰናበቱት ስለዚህ ስንብቱ ህጋዊ ነው ሲል ተከራክረዋል፡፡
 የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የቀረበለትን ዳይ ካለው ሕግ እና ማስረጃ ጋር በማገናዘብ በመመርመር ተጠሪ አመልካች ፈፅሞታል የሚለውን ጥፋት በሠነድም ሆነ በሰው በማስረጃ አላስረዳም፡፡ ስለዚህ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ሲል የአመልካች ወደ ሥራ የመመለስን ጥያቄ አስመልክቶ ለድርጅቱ ሠላማዊ ግንኙነትና ችግር እንዳይፈጠር ሲባል ቢሰናበቱ ይሻላል በማለት የ6 ወር የካሣ ክፍያ ተከፍሏቸው ይሠናበቱ ሲል ወስኗል፡፡ አመልካችም በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት የይግባኝ አቤቱታቸውን ለፌዴራ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቧል፡፡ ፍ/ቤቱም የግራቀኙን በማከራከር አመልካች ፈጠሩ የተባለው ጥፋት በአዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 27 ሥር የሚሸፈን ያለመሆኑን እና አመልካች ወደ ሥራቸው ቢመለሱ በአሰሪውና ሰራተኛ ሰላማዊ የስራ ግንኙነት ይኖራል ተብሎ አይገመትም በማለት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን በፍ////348(1) መሠረት አፅንቶታል፡፡
 የሠበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ላይ ነው፡፡ አመልካች በ16/7/2001 ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጡት ውሣኔዎች መሠረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመባቸው ነው በማለት አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ይህ የሰበር ችሎትም አቤቱታውን መሠረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቷል፡፡ ዳዩ በሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው የሥር ፍ/ቤት ስንብቱ ህገወጥ ነው ካለ በኋላ ለአመልካች ሊከፈላቸው የሚገባው የካሣ ክፍያ ብቻ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ ከአዋጅ ቁ 377/96 አንቀፅ 43(4) አኳያ ለመመርመር ነው፡፡ በዚህም መሠረት ይህን ነጥብ ግራቀኙ ካሰሙት ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህ ጋር አገናዝበን መርምረናል፡፡
 እኛም የዳዩን አመጣጥ ጠቅለል አድርገን ስናየው አመልካች በተጠሪ ድርጅት በመምህርነት ሲያገለግ ቆይተው ተጠሪ ሕገወጥ ድርጊትና የባሕርይ ችግር አሳይቷል በማለት በመሰናበታቸው ምክንያት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራቀኙን በማከራከር የአመልካች ስንብት ህገወጥ ነው ሲል ለድርጅቱ ሠላም ሲባል አመልካች ወደ ሥራ ሊመለሱ አይገባም የ6 ወር ካሣ ተከፍሏቸው ይሠናበቱ ሲል ወስኗል፡፡
 ዳዩን በይግባኝ ያየው የፌዴራ ከ//ቤትም ግራቀኙን በማከራከር የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ አፅንቶታል፡፡ በእኛም በኩል ከሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ እና የግራቀኙ በሰበር ችሎት ባካሄዱት ክርክር መረዳት እንደተቻለው የአመልካችን ስንብት አስመልክቶ ሕገወጥ ነው መባንና ለድርጅቱ ሰላም ከፍተኛ ችግር እንዳይፈጠር ሲባል አመልካች ወደሥራ ሊመለሱ አይገባም መባ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ምክንያቱም የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ቅሬታን ከፈጠረ የመማር ማስተማሩ ሂደቱን ከግብ ሊያደርሰው ይችላል ተብሎ ስለማይተማመን በተማሪዎችም ላይ ተፅኖ ሊፈጥር የሚችል ስለሆነ ነው፡፡ ባጠቃላይ በሕ መሠረት ለአመልካች ሊከፈላቸው የተወሰነው የ6 ወር የካሣ ክፍያ ሌሎች በሕ የተቀመጡትን ክፍያዎች ሊያስቀረው ይችላል? የሚትም ነጥብ መታየት ያለበት ነጥብ ሆኖ በመገኘቱ በአዋጅ 377/96 አንቀፅ 43(4) መሠረት አመልካች ሊከፈላቸው የሚገቡ ክፍያዎች እንዳ ለመረዳት አያዳግትም፡፡ ተጠሪም በበኩ በሰበር ችሎቱ በሰጠው መልስ አመልካች ሊከፍላቸው የሚገባ ተጨማሪ ክፍያ እንዳላቸው አምኖ ተከራክረዋል፡፡ በዚህም መሠረት በሥር ፍ/ቤቶች የስንብቱ ውጤት የሆኑት በሕ የተቀመጡት ክፍያ በ‘6’ ወር ካሣ ብቻ ተወስኖ ሌላው ጥቅማቸው መታለፉ አግባብ ያለው ሆኖ አላገኘነውም፡፡

ው ሣ ኔ
1. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.25807 በቀን                 እና  ተሻሽለዋል ይፃፍ፡፡
2. አመልካች በአገልግሎት ዘመናቸው የተቀመጠላቸው የፕሮቪደንት ክፍያ የ2 ወር
  የማስጠንቀቂያ እና የምስክር ወረቀት ሊሰጣቸው ይገባል ብለናል፡፡
3. ግራ ቀኙ የወጪና ኪሣራ ይቻቻ፡፡
4. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡


/

No comments:

Post a Comment