Saturday, March 7, 2020

የሰበር መ/ቁ. 41058 የአሰሪ ድርጅት ለ3ኛ ወገን መተላለፍ በሰራተኛው ላይ ያለው ውጤት


የሰበር መ/. 41058
የካቲት 17 ቀን 2ዐዐ1 .
ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ
  ሐጎስ ወልዱ
  ሂሩት መለሠ
  በላቸው አንሺሶ
  ሱልጣን አባተማም
አመልካች፡- አርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት ሃዋሣ ቅርንጫፍ - ማቲያስ ግርማ
     /ነገረ - ፈጅ/ ቀረበ፡፡
ተጠሪ፡- አቶ ዳንሴ ምትኩ - አልቀረቡም
ፍ ር ድ
 በበኩላችንም አመልካች ጥቅምት 13 ቀን 2ዐዐ1 .ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል፡፡ አቤቱታው በሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው ሰንብቱ ሕገወጥ ነው ተብሎ ለተጠሪ የስድስት ዓመት የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፈል በሚል የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ለመመርመር ነው፡፡ በዚህ መሠረትም ይህን ነጥብ ከተደረገው ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕ ጋር አገናዝበን መርምረናል፡፡

 ከስር ጀመሮ ከተደረገው ክርክር ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ ቀደም ሲል ተቀጥሮ የነበረው በልማት ባንክ በመያዣነት ተይዞ የነበረው ሕንፃ ባንኩ እስከሚሸጠው ድረስ በጥበቃ ሠራተኛነት ለማገልገል ነው፡፡ በኋላ በተደረገው የሐራጅ ሽያጭም  አመልካች ሕንፃውን ገዝቶአል፡፡ ከዚህ በኋላም በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ውል ተደርጎ ተጠሪ ለአንድ ዓመት የጥበቃ ስራ ሰርቶአል፡፡ አመልካች የስራ ው የተቋረጠው በው መሠረት በመሆኑ ከሕግ ውጪ ነው ሊባል አይገባም በማለት የተከራከረውም ይህን ምክንያት በመስጠት ነው፡፡ ለሰበር ችሎት ባቀረበው አቤቱታ የጠየቀው ዳኝነት ተጠሪ በልማት ባንክ ተቀጥሮ ለሠራባቸው አምስት ዓመታት ጭምር የአገልግሎት ክፍያ እንድከፍል የተሰጠው ውሣኔ ይሻርልኝ የሚል በመሆኑ የስንብቱ ሕጋዊ መሆን አለመሆን በተመለከተ የሚሰጥ ውሣኔ አይኖርም፡፡ ተጠሪ ክፍያውን በሚመለከት ያቀረበው ክርክር በእርግጥም አመልካች ቀጥሮ አሠርቶኛል የሚል ሣይሆን፣ ሕንፃውን ሲገዛ የእኔንም መብት አብሮ ገዝቶአል የሚል ነው፡፡ የስር ፍ/ቤቶችን በዚህ መልክ ከተጠሪ የቀረበውን ክርክር በመቀጠል ነው የወሰኑት፡፡
 የተያዘው ዳይ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የተነሣውን ክርክር የሚመለከት በመሆኑ መወሰን ያለበት በአሠሪና ሠራተኛ ዳይ አዋጅ ቁ. 377/96 እና በግራ ቀኝ ወገኖች ውል መሠረት ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደተገለፀው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረው የስራ ውል ለአንድ ዓመት የሚቆይ ነው፡፡ ይህም ማለት ተጠሪ ለአመልካች አገልግሎት የሰጠው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው አመልካች ሕንፃውን ሲገዛ የልማት ባንክን ግዴታም ሆነ መብት አልተላለፈለትም፡፡ ተጠሪን ከሕንፃው ጋር አብሮ የመረከብ ግዴታ የሚፈጥር ሕግም ሆነ ውል የለም፡፡ ተጠሪን ለአንድ ዓመት የቀጠረው በራሱ ፈቃድ ነው ስለዚህም ግዴታ ቢኖርበት ው ከተደረገ በኋላ ያለውን ጊዜ ብቻ የሚመለከት ነው የሚሆነው፡፡ አመልካች የልማት ባንክን መብትና ግዴታ መረከቡ የግድ ነው የሚለው የስር ፍ/ቤት ትችት የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር መሠረት የለውም፡፡ ሲጠቃለል አመልካች የልማት ባንክን ግዴታ የሚሸከምበት የሕግ መሠረት ስለሌለ አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል፡፡
ው ሣ ኔ
1.
የአዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ችሎት በመ/. 13279 ግንቦት 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በደቡብ ብ/////የአዋሣ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.. 581 ሰኔ 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የክል ጠ//ቤት በመ.. 22826 መስከረም 22 ቀን 2ዐዐ1 .ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ////ሕግ ቁ. 348/1/ መሠረት ተሻሽለዋል፡፡
2.
አመልካች ለተጠሪ መክፈል ያለበት በውል ቀጥሮ ላሰራው ለአንድ ዓመት በቻ ነው ብለናል፡፡

3.
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻ፡፡ መዝገቡ ይመለስ፡፡
የማይነበብ ምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
.


No comments:

Post a Comment