Friday, March 6, 2020

የህግ ቃላት ትርጓሜ-የእንስሳት መደሀኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 728-2004


የእንስሳት መደሀኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 728-2004

“እንስሳ” ማለት ለማዳና የዱር እንስሳትን፣ አዕዋፍን፣ የውሃ ውስጥ እንስሳትን፣ ንብንና የሐር ትልን ያጠቃልላል፤
2/“የእንስሳት መድኃኒት” ማለት የእንስሳት በሽ ታን ለመመርመር፣ ለማከም ወይም ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውል ማንኛውም ንጥረ ነገር ወይም የንጥረ ነገሮች ውህድ ሲሆን የውስጥና የውጭ ጥገኞችንና በሽታ አስተላላፊ ተባዮችን ማከሚያ ውህዶችን፣ ባዮሎጂካል ውጤቶችን፣ የሳኒተሪ መገልገያዎችንና የእንስሳት ሕክምና መሣሪያዎችን ያካትታል፤
3/“ባዮሎጂካል ውጤት” ማለት ሪኤጄንት፣ የደም ተዋፆ፣ የተዳከመ ወይም የሞተ ክትባት ወይም የጀርም ጄኔቲክ ውጤት ሆኖ የእንስሳት በሽታን ለመመርመር፣ ለመከ ላከል ወይም ለማከም ተግባር የሚውል ነው፤

4/“የእንስሳት ሕክምና መሣሪያ” ማለት የእን ስሳት በሽታን ለመመርመር ወይም ለማከም ጥቅም ላይ የሚውል መሣሪያ ሲሆን የላቦራ ቶሪ፣ የማዳቀያና የማኮላሻ መሣሪያዎችን ያካትታል፤
5/“ባህላዊ የእንስሳት መድኃኒት” ማለት በል ምድ የዳበረ፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባ ይነት ያገኘ እና በሙከራ የተረጋገጠ የእንስሳት መድኃኒት ነው፤
6/“ተደጋጋፊ ወይም አማራጭ የእንስሳት መድኃኒት” ማለት ከባህላዊ ወይም ከዘመ ናዊ የእንስሳት ጤና ሥርዓት ጋር ያልተጣ መረ ሆኖ በተደጋጋፊነት ወይም በአማራ ጭነት ጥቅም ላይ የሚውል የእንስሳት መድ ኃኒት ነው፤
“ጀርም” ማለት ማንኛውም የበሽታ መንስኤ ተህዋስያን ሲሆን ቫይረስን፣ ባክቴሪያን፣ ፈንገስን፣ ፕሮቶዞዋንና የውጭና የው ስጥ ጥገኞችን ያካትታል፤
8/“ፋርማኮቪጂላንስ” ማለት ከእንስሳት ጤና ባለሙያዎችና ከእንስሳት ባለቤቶች መረጃ በማሰባሰብና በመመራመር የእንስሳት መድ ኃኒት በታካሚው እንስሳ ላይ የሚያስከት ለውን ጉዳት ማጥናት ነው፤
9/“የእንስሳት መድኃኒት ንግድ” ማለት የእንስ ሳት መድኃኒት ለትርፍ ዓላማ ማምረት፣ እንደገና ማሸግ፣ ከውጭ አገር ማስመጣት፣ ወደውጭ አገር መላክ፣ በጅምላ ማከፋፈል ወይም በችርቻሮ ማደል ሲሆን የእንስሳት መድኃኒት ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ አገልግሎትን እና በንግድ ወኪልነት መሥራትን ይጨምራል፤
0/“መኖ” ማለት ለንግድ ዓላማ የተመረተ ወይም የተዘጋጀ የእንስሳት ምግብ ነው፤
01/“የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገር” ማለት በይዘቱ ምግብነት ያለው ወይም የሌለው ሆኖ መኖው በሚዘጋጅበት ጊዜ በመኖ ውስጥ በጥቂት መጠን የሚጨመር ንጥረ ነገር ነው፤
02/“የመኖ ንግድ” ማለት መኖን ለንግድ ማዘጋጀት፣ ማሸግ፣ ከውጭ ማስመጣት፣
ወደ ውጭ መላክ ወይም በጅምላ ወይም በችርቻሮ መሸጥ ሲሆን የመኖ ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ አገልግሎትን እና
በንግድ ወኪልነት መስራትን ይጨምራል፤
03/“የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” ማለት ባለሥልጣኑ ያወጣውን መሥፈርት በማሟላት በእንስሳት መድኃኒት ወይም መኖ ንግድ ለመሰማራት ብቁ መሆንን የሚያረጋግጥ አግባብ ባለው አካል የሚ ሰጥ የምስክር ወረቀት ነው፤
04/“ማሸጊያ” ማለት የእንስሳት መድኃኒትን ወይም መኖ በውስጡ ለመሙላት፣ ለመክ ተት ወይም ለመጠቅለል የሚያገለግል ማንኛውም መያዣ ነው፤
05/“ገላጭ ፅሁፍ” ማለት ማንኛውም በማሸ ጊያ ላይ የተፃፈ ወይም የተለጠፈና ስለእን ስሳት መድኃኒት ወይም ስለመኖ ተገቢ ውን መረጃ የሚሰጥ መግለጫ ሲሆን በማሸ ጊያው ውስጥ በአባሪነት የሚከተተውን ጽሑፍ ይጨምራል፤
“አስመስሎ ማቅረብ” ማለት የአንድን አም ራች እውነተኛ ምርት ማሸጊያ፣ የንግድ ስም፣ የንግድ ምልክት ወይም ማንኛ ውንም ዓይነት ልዩ ምልክት በመጠቀም የእንስሳት መድኃኒትን ወይም መኖን በእውነተኛው አምራች እንደተመረተ በማ ስመሰል አሽጎና ገላጭ ጽሑፍ አድርጎ ማቅረብ ነው፤
07/“መከለስ” ማለት የእንስሳት መድኃኒት ወይም መኖ ከተሰራበት ንጥረ ነገር ውጭ ከሌላ ነገር ጋር በመደባለቅ ወይም የተሰራበትን ንጥረ ነገር በሙሉ ወይም በከፊል በሌላ በመተካት ወይም ንፅህና በጐደለው መንገድ መድኃኒቱን ወይም መኖውን በማዘጋጀት ወይም በማከማቸት በባዕድ ነገሮች እንዲበከል አድርጐ ጥራቱን መቀነስ ነው፤
08/“ቅድመ ክሊኒካል ሙከራ” ማለት የእንስ ሳት መድኃኒትን፣ መኖን ወይም የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገርን በሚመለከት የሚከናወን የሰነድ ምርመራ፣ አካላዊ ምልከታና የላቦራቶሪ ምርመራ ነው፤
09/“ክሊኒካል ሙከራ” ማለት የእንስሳት መድኃኒት ፈዋሽነትና ደህንነት ለማረጋ ገጥ
በእንስሳት ላይ የሚከናወን ሙከራ ነው፤
!/“የእንስሳት መድኃኒት ባለሙያ” ማለት የእንስሳት ሃኪም ወይም ረዳት የእንስሳት ሃኪም ወይም ከእንስሳት መድኃኒት ጋር የተያያዘ የሙያ አገልግሎት የሚሰጥ የእንስሳት ጤና ፋርማሲስት፣ የእንስሳት ጤና ድራጊስት ወይም የእንስሳት ጤና ፋርማሲ ቴክኒሽያን ነው፤
!1/“የእንስሳት ሐኪም” ማለት ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ በእንስሳት ህክምና ሙያ ዶክትሬት ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ የተመረቀ ነው፤
!2///
/ “ሌሎች የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች” ማለት ከታወቀ ተቋም በእንስሳት ህክምና ሙያ በቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪ ወይም በዲፕሎማ ወይም በሰርተፍኬት የተመረቀ ነው፤
!3///
/ “የሙያ ፈቃድ” ማለት የእንስሳት መድኃ
ኒት ባለሙያ ወይም የእንስሳት መኖ
ባለሙያ በሙያው መሥራት እንዲችል አግባብ ባለው አካል የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነው፣
!4/“የእንስሳት መድኃኒት ቤት” ማለት የእን ስሳት መድኃኒት ብቻ የሚሸጥበት ተቋም ነው፤
“የእንስሳት መኖ መሸጫ” ማለት የእንስ ሳት መኖ፣ የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገርና የመኖ ዘር ብቻ የሚሸጥበት ተቋም ነው፤
!6/ “የእንስሳት መኖ ባለሙያ” ማለት ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ ወይም ተቋም በእንስሳት ሳይንስ ወይም በእንስሳት መኖና ግጦሽ በዲፕሎማ ወይም በመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ የተመረቀና በተጨማሪ የመኖና የእንስሳት ስነምግብ ስልጠና የወሰደ ነው፤
!7/“ማስታወቂያ” ማለት ማንኛውንም ማስገን ዘቢያ፣ ሰርኩለር፣ መግለጫ ጽሑፍ ወይም ሌላ መሰል ሰነድና በቃል፣ በምስል ወይም በድምፅ የተላለፈን መልዕክት ያካትታል፤
!8/ “ሚኒስቴር” ማለት የግብርና ሚኒስቴር ነው፤
!9/“ባለሥልጣን” ማለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ የሚቋቋም የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው፤
"/“አግባብ ያለው አካል” ማለት እንደ አግባቡ ባለሥልጣኑ ወይም የእንስሳት መድኃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ተግባራትን የማከናወን ስልጣን የተሰጠው የክልል መንግሥት አካል ነው፤
"1/ “ስልጣን የተሰጠው አካል” ማለት የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ነው፤
"2/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ #7/1/ የተመለከተው ማንኛውም ክልል ሲሆን የአዲስ አበባንና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችን ይጨምራል፤
"3/ “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፤

No comments:

Post a Comment