Monday, March 9, 2020

በፖስታ አገልግሎት ድርጅት እንዳይተላለፉ የተከለከሉ መልዕክቶች


.በፖስታ አገልግሎት ድርጅት እንዳይተላለፉ የተከለከሉ መልዕክቶች


  • በተፈጥሯቸው ወይም በአጠቃለላቸው በፖስታ ሠራተኞች ላይ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ወይም አብረው የሚላኩ ሌሎች ዕቃዎችን ሊያበላሹ ወይም ሊጎዱ የሚችሉ፣
  • የሚፈነዱ፣ በቀላሉ የሚቀጣጠሉ  ወይም ራዲዮአክቲቭ የሆኑ እና ሌሎች ጎጂ ዕቃዎች
  • አዳይ አገር (ፖስታ ቤት) የማይቀበላቸው ነገሮች ሁሉ፣
  • ከንብ፣ ከአልቅት፣ ከሐር ትል በቀር፤ ለመላክና ለመቀበል የተፈቀደላቸው ድርጅቶች ከሚልኳቸውና ከሚቀበሏቸው ተባዮችና አጥፊ ነፍሣትን ለማጥፋት ከሚያገለግሉ ነፍሣት በቀር፤ (በህግ እንደተወሰነው መግባት ከሚፈቀድላቸው እንስሶች) በስተቀር ማንኛውም ሕይወት ያላቸው እንስሶች፤
  • ለህክምና ጉዳይ ሲባል ለመላክና ለመቀበል የተፈቀደላቸው ድርጅቶች ከሚልኩት በስተቀር እንደ ሐሺሽ፣ ሞርፌን፣ ሔሮይን፣ ኮኬይንና ሌሎች የናርኮቲክ ፀባይ ያላቸው ነገሮች፣
  •  ከመልካም ስነምግባር ሞራልና ባህል ጋር ተቃራኒ የሆኑ ጽሑፎች፣ ምስሎች ወይም በድምጽ የተቀረጹ ነገሮች
  • ወርቅ ብር ነሀስ የብር ኖቶች ሣንቲሞችና የባንክ ኖቶች …….ወዘተ፣
  • በዓለምና አገር አቀፍ ደረጃ በሕግ የተከለከሉ ነገሮች በሙሉ፣

No comments:

Post a Comment