Tuesday, August 25, 2020

የሥራ ውል መቋረጥ-ወደ ሥራ መመለስ--ቦነስና የደመወዝ ጭማሪ--ሰ/መ/ቁ. 338814

 የሰ/መ/ቁ. 338814

የካቲት 3 ቀን 2ዐዐ1

ዳኞች፡- አብዱልቃድር መሐመድ

       ሐጎስ ወልዱ

       ታፈሰ ይርጋ

       በላቸው አንሺሶ

       ሱልጣን አባተማም

አመልካች፡- ኢካፍስ አ/ማ አቶ ታዬ ብርሃኑ ጠበቃ ቀረቡ፡፡

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሰላማዊት ብርሃኑ - አልቀረበችም፡፡

      መዝገቡን መረምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍ ር ድ

      በዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ክርክር የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሆኖ ከሣሽ ተጠሪ ነበሩ አመልካች ደግመ ተከሣሽ ነበር፡፡ ክሱም አመልካች ያለአግባብ ከሥራ አሰናብቶኝ በፍ/ቤት ውሣነ የ5 ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎኝ ወደ ሥራ ተመልሼያለሁ፡፡ ከሥራ ተሰናብቼ በነበረበት ወቅት ለሠራተኞች የተፈቀደው የደመወዝ ጭማሪና አልሆነምና እንዱከፈለኝነ ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡

      አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ክሱ በይርጋ ይታገዳል በድርጅቱ ኀብረት ስምምነት መሠረት በበጀት ዓመቱ ለ9 ወራት ያሕል መሥራትና የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤትም ከ5ዐ በላይ መሆን አለበት፡፡ ከሣሽ ሥራ ላይ ስላልነበሩ ሥራ አፈኀፀምም ስላልተመላላቸው ክፍያ አየገኙም በማለት ተከራክሯል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የዓመት እረፍት ጊዜ ክፍያ በስተቀር ሌሎች በክሱ የተጠየቀውን የክፍያ ጥያቄዎች በሙሉ ውድቅ በማድረግ ሊከፈላቸው አይገባም ሲል ወስኗል፡፡ በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 67ዐ89 በሆነው ሰኔ 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት የደመወዘ ጭማሪ እና የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲከፈላቸው በማለት ወስኗል፡፡

      የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው፡፡ እኛም አመልካች ሰኔ 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ የቀረበው ቅሬታ መሠረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ሰምተናል፡፡ አቤቱታው በዚህ ችሎት እንዲታይ ያስቀርባል የተባለበት ነጥብ የደመወዘ ጭማሪና የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲከፈል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ነው፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ ግራ ቀኙን ጥር 19 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ክርክር አካሂደዋል፡፡

      የግራ ቀኙን ክርክር እኛም አግባብ ካለው ሕግ ጋር ለማገናዘብ መረምረናል፡፡

      ተጠሪ የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲከፈላቸው የጠየቁትን በተመለተ በውሉ መሠረት አሁንም በድርጅቱ በማገልገል ላይ ያሉ በመሆናቸውና አመልካች ያላስተባበለ በመሆኑ የትምህርት ቤት ክፍያ እንዲከፈላቸው የከፍተኛው ፍ/ቤት የወሰነው ጭማሪ እንዲከፈላቸው የተሰጠውን ውሣኔ አግባብነት ስንመረምረው ተጠሪ የደመወዝ ጭማሪ እንዲከፈላቸው በጠማየቁበት በጀት ዓመት ውሰጥ ለ9 ወራት ያሕል ሥራ ላይ አልነበሩም፡፡ በሥራ ላይ ነበርኩ ወይም በሥራ ላይ ያልነበርኩበት ጊዜ ከ9 ወራት ያነሰ ጊዜ ነው ብለውም አልተከራከሩም፡፡ ይህ ከሆነ በኀብረት ስምምነት አንቀፍጽ 22 እና 32 /1፣2/ ላይ እንደተመለከተው ለ9 ወራት ያሕል ጊዜ በሥራው ላይ ያልተገኘና የሥራ አፈፃፀሙ 5ዐ% በላይ ያልሆነ ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ እንደማይሰጠው ተመልክቷል፡፡ የከፍተኛው ፍ/ቤት ለውሣኔው መሠረት ያደረገው በኀብረት ስምምነቱ ያልተመለከተውን ምክንያት መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ይኸውም በፍ/ቤት ክርክር ከተደረገ በኋላ ወደ ሥራ እንዲመለሱ መወሰኑን ተሪ በሥራ ላይ ሊገኙ ያልቻሉት አመልካች ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ የሥራ ውል ማቋረጡ በፍርድ ተረጋግጧል በማለት ነው፡፡ በድርጅቱ ኀብረት ስምምነተ ከላይ በተጠቀሱ ድንጋጌዎች በግልጽ እንደተመለከተው በበጀት ዓመት ለ9 ወራት ያሕልና የሥራ አፈፃፀሙ 5ዐ% እና በላይ ያልሆነ ሠራተኛ ቦነስና የደማወዝ ጭማሪ የማይሰጠው መሆኑን ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግመ ድንጋጌው ሌላ ትርጉም የሚሠጠው አይሆንም፡፡ የሕብረት ስምምነቱ ለደመወዝና ለሌላ ጥቅማ ጥቅም ክፍያ አከፋፈል በግልጽ ከተመለከተው ከሕብረት ስምምነቱ ውጪ የሥራ ውሉ የተቋረጠው ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ነው ወይንስ አይደለም የሚለው ነጥብ እንደ ጭብጥ ተይዞ ውሣኔ መስጠቱ ለተያዘው ጉዳይ ተገቢንት የሌለ ነው፡፡ በመሆኑም ተጠሪ የጠየቁትን የደመወዝ ጭማሪ ሊከፈላቸው ይገባል በማለት በከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሠረዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል፡፡

ው ሣ ኔ

  1. የከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 67ዐ89 ሰኔ 12 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችሎት የደመወዝ ጭማሪ በሁለት ጊዜ የተደረገውን እንዲከፈላቸው ሲል የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሠረት ተሽሯል፡፡
  2. የት/ም ቤት ክፍያ እንዲከፈላቸው የተሰጠው ውሣኔ ፀንቷል፡፡
  3. ተጠሪ የጠየቁት የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ እንዲያገኙ የሚደረግበት የሕግ ምክንያት የለም በለት ተወስኗል፡፡
  4. ወጭና ኪሣራ የዚህ ፍ/ቤትን ግራ ቀኙ ይቻቻሉ ብለናል፡፡

መዝገቡን ዘግተናል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

 

 

ነ/ዓ

No comments:

Post a Comment