Saturday, February 27, 2021

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 52-1992

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፶፯/፲፱፻፺፪

የፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር /፲፱፻፹፯ አንቀጽ መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡


አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ ‹‹ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች የሥነ ምግባር ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፶፯/፲፱፻፺፪›› ተብሎ ሊተቀስ ይችላል፡፡

የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ ደንብ የፌዴራል ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ በተሰጠው በማንኛውም ሰው ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አጠቃላይ መርህ
ማንኛውም ጠበቃ ሕግን ለማስበርና ፍትሕን ለማስገኘት የፍትሕ አስተዳደሩን የማገዝ ኃላፊነት አለበት፡፡ ማንኛውም ጠበቃ በተለይም ለደንበኛው ለሌሎች የሕግ ሙያተኞችና ተከራካሪ ወገኖች ለፍርድ ቤት ለሙያው እና በአጠቃላይ ለህብረተሰቡ ያለበትን የሙያ ኃላፊነት በቅንነት በታማኝነት እና በእውነተኛነት መወጣት አለበት፡፡

ደንበኛ ስለመቀበል
ማንኛውም ጠበቃ የሕግ አገልግሎት ለማግኘት የመጣ ደንበኛን ጉዳይ ተቀብሎ የጉዳዩን  ፍሬ ነገርና ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ክርክሩ ሕጋዊ መሠረት የሌለው ከሆነ ጉዳዩን መያዝ የለበትም፡፡ ሆኖም ለሰጠው የሕግ ምክር አገልግሎት ተገቢውን ክፍያ ተቀብሎ ደንበኛው ያሰናብታል፡፡

. አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ስላለመሆን
ማንኛውም ጠበቃ በአገልግሎት ጠያቂ ደንበኛው የሞራል ባህሪ በተፈፀመው ወንጀል ከባድነትና አስነዋሪነት ወይም በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ነው በሚል እምነት ወይም የደንበኛውን የፖለቲካ የኢኮኖሚ የማኅበራዊ ወይም የሞራል አቋሙን መሠረት በማድረግ የጥብቅና አገልግሎት አልሰጥም ማለት አይችልም፡፡

ከደንበኛ ጋር ስለሚደረግ ውል
. ማንኛው ጠበቃ ከደንበኛው ጋር በጽሑፍ የሰፈረ ግልጽ የውል ስምምነት ሊፈጽም ይገባል፡፡ ውሉም የተዋዋዩችን ስም አድራሻ የአገልግሎቱን ዓይነት የውክልና ዓይነትና መጠን አገልግት ክፍያውን መጠን ክፍያው የሚወሰንበትን ሥልትና አከፋፈሉን መጠን ክፍያው የሚወሰንበትን ሥልትና አከፋፈሉን ሥርዓትና የመክፍያውን ጊዜ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን የያዘ ይሆናል፡፡
. አንድ ጠበቃ ለደንበኛው የገባውን የሙያ አገልግሎት በአግባቡ ባለማበርከቱ ምክንያት የሚኖርበትን የፍትሐብሔር ኃላፊነት የሚቀንስ ወይም የሚያስቀር ስምምነት ዋጋ የለውም፡፡

. የአገልግሎት ዓይነትና የውክልና መጠን
. ማንኛውም ጠበቃ የደነበኛውን ጉዳይ ፍሬ ነገርና ማስረጃዎች ከመረመረ በኃላ በሕግ መሠረት በጉደዳዩ ሊገኝ የሚችለውን ውጤት ወይም አማራጭ ውጤቶች እንዲሁም ተፈላጊውን ውጤት ለማግኘት ደንበኛው ለጠበቃው ሊሰጠው የሚገባውን የውክልና ዓይነትና መጠን በማስረዳት ከተገቢው ውሳኔ ላይ እንዲደርስ የመርዳት ግዴታ አለበት፡፡
. ደንበኛው ከጠበቃው በተሰጠው የሕግ ምክር ላይ ተመስርቶ የሚሰጠው ውሳኔ ሕግንና ይህን ደንብ የማይጥስ እስከሆነ ድረስ ጠበቃው የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ በተለይም ጉዳዩ በግልግል እንዲያልቅ ደንበኛው ከወሰነ ጠበቃው ውሳኔውን ማክበር አለበት፡፡
. ደንበኛው የሚፈልገው የዕርዳታ ወይም የአገልግሎት ጥያቄ ይህን የሥነ-ምግባር ደንብ ወይም ሌላ ሕግ ሚየጥስ ከሆነ ጠበቃው አገልግሎቱን ሊሰጥ ማይችልበትን ምክንያት ለደንበኛው ማስረዳትና ደንበኛው ምክሩን ተቀብሎ የማያስተካክል ከሆነ ማሰናበት አለበት፡፡
. ደንበኛው በውክልናው ላይ ውሳኔ ለመስጠት በመፈለግ መረጃ በጠየቀ ጊዜ ጠበቃው ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችሉትን መረጃዎች በማቅረብ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ መርዳት አለበት፡፡

ብቃት ያለው አገልግሎት ስለመስጠት
. ማንኛውም ጠበቃ በሚሰጠው የጥብቅና አገልግሎት ከፍተኛ የሙያ ችሎታና ብቃት ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡
. ጠበቃው ሕግ በሚፈቅደው መሠረት
) የደንበኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር ዕውቀቱና የሥራ ልምዱን በሥራ ላይ የማዋል፤
) የደንበኛውን ጉዳይ በትጋት የመከታተልና አፋጣኝና ፍትሐዊ ውሣኔ በትጋት የመከታተልና አፋጣኝና ፍትሐዊ ውሣኔ ለማግኘት ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ ሁሉ በጥንቃቄ በወቅቱ የመፈጸም ሙያዊ ግዴታ አለበት፡፡

. አስፈላጊውን መረጃ ስለመስጠት
ማንኛውም ጠበቃ ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃና የሚገኝበትን ሁኔታ በየጊዜው ለደንበኛው የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ ደንበኛው መረጃ እንዲሰጠው በጠየቀ ጊዜም አፋጣኝ ምላሽ የማግኘት መብት አለው፡፡

. ምስጢር ስለመጠበቅ
. ማንኛውም ጠበቃ የደንበኛውን ግላዊ ወይም ድርጅታዊ መረጃ ወይም በሙያ አገልግሎቱ ምክንያት በእጁ የገባውን ማንኛውም ሌላ መረጃ በምስጢር የመጠበቅ ሙያዊ ግዴታ አለበት፡፡
.ጠበቃው በውክልናው ምክንያት ከደንበኛው የተሰጠውን መረጃ እና ማንኛውንም ሌላ መረጃ ከደንበኛው ፈቃድ ሳያገኝ ሊገልጽ አይችልም፡፡
. የጠበቃ ምስጢር የመጠበቅ ሙያዊ ግዴታ በእርሱና በደንበኛው መካከል የነበረው የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት ቀሪ ሊሆን አይችልም፡፡

፲፩. ምስጢር ስለሚገለጽበት ሁኔታ
የአንቀፅ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ጠበቃው ተገቢ ነው ብሎ ሲያምን በሙያ ሥራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን መረጃ በሚከተሉት ምክንያቶች እንደአስፈላጊነቱ መጠን ሊገልጽ ይችላል
. ከደንበኛው ያገኘው መረጃ ለተወከለበት ሥራ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ
. ከደንበኛው ጋር ክርክር በሚፈጠርበት ጊዜ ራሱን ለመከላከል ወይም መብቱን ለማስከበር
. የውክልና ሥልጣኑን የተመለከተ ክርክር ሲነሳ ወይም
. ሕግ በሌላ ሁኔታ በግልጽ የጣለበትን ግዴታ ለመወጣት፡፡

፲፪. የጥቅም ግጭት
ማንኛውም ጠበቃ በራሱና በደንበኛው ወይም በዘመዶቹና በደንበኛው ወይም በሸሪኮቹና በደንበኛው ወይም በሁለት ደንበኞቹ መካከል የጥቅም ግጭት መኖሩን እያወቀ የሙያ አገልግሎት ለመስጠት መዋዋል አይችልም፡፡ የጥቅም ግጭት መኖሩ የታወቀው አገልግሎቱ ከተጀመረ በኋላ ከሆነ ይሄንኑ ለደንበኛው አስረድቶ አገልግሎቱን ማቋረጥ አለበት፡፡

፲፫. ከቀድሞ ደንበኛ ጋር ስለሚኖር የጥቅም ግጭት
. ማንኛውም ጠበቃ ከዚህ ቀደም የጥብቅና አገልግሎት ከሰጠበት ጉዳይ ወይም ከደንበኛው ጥቅም ጋር በሚፃረሩ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከቀድሞ ደንበኛው ጋር ተመካክሮ የጽሑፍ ፈቃድ ካላገኘ በስተቀር ለአዲስ ደንበኛ የጥብቅና አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ከዚህ ቀደም ይሰራበት የነበረው የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት የጥብቅና አለግሎት ከሰጠው ደንበኛ ጥቅም ጋር የሚጻረር ጥቅም ላለውና ስለደንበኛው መረጃ ባገኘበት ጉዳይ ከቀድሞ የድርጅቱ ደንበኛ ጋር ተመካክሮ የጽሑፍ ፈቃድ ካላገኘ በስተቀር ለአዲሱ ደንበኛው የጥብቅና አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም፡፡

፲፬. በጠበቃና በደንበኛ መካከል የሚፈጸሙ ውሎች
ማንኛውም ጠበቃ ከደንበኛው ጋር ማናቸውንም ውል ሊዋዋል የሚችለው ከዚህበታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ከተሟሉ ብቻ ነው፡፡
. በጠበቃውና በደንበኛው መካከል የሚደረገው ውል ከወቅቱና ከሁኔታዎች አንፃር ተገቢና ምክንያታዊ ሲሆን
. ጠበቃው የስምምነቶቹን መስፈርቶችና የውሉን ዓይነት ለደንበኛው በግልጽ ያስረዳው ከሆነ ወይም
. ደንበኛው በውሉ ላይ ከሌላ ሰው ጋር ተመካክሮ ስምምነቱን በጽሑፍ ያፀደቀ ሲሆን፡፡

፲፭. ከደንበኛው ስለሚደረግ ስጦታና ኑዛዜ
ማንኛውም ጠበቃ ደንበኛው በመልካም ፈቃዱ የሚያደርግለትን ኑዛዜ ወይም ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ስጦታ ሊቀበል የሚችለው ጉዳዩ በጽሑፍ ከሆነና ድርጊቱ በሚፈጸምበት ጊዜ ደንበኛው ተገቢው የምክር አገልግሎት የተሰጠውና ስለድርጊቱም ውጤት ከገለልተኛ ጠበቃ የተረዳ መሆኑን ካረጋገጠ ብቻ ነው፡፡

፲፮. በጠበቃና በደንበኛ መካከል ስለሚደረግ ብድር
ማንኛውም ጠበቃ ከደንበኛው ገንዘብ ሊበደር ወይም ለደንበኛው ገንዘብ ሊያበድር አይችልም::

፲፯. ጠበቃ ሸሪክ በሆነበት የንግድ ድርጅት ስለሚሰጠው የምክር አገልግሎት
ማንኛውም ጠበቃ ሸሪክ በሆነበት የንግድ ድርጅት ውስጥ አጠቃላይ የንግድ ድርጅቱን ወይም ሦስተኛ ወገኖችን በተመለከተ የምክር አገልግሎት ለመስጠት ይችላል፡፡ ሆኖም ራሱን በሚመለከት የድርጅቱ ጉዳይ ላይ የምክር አገልግሎት ለመስጠት አይችልም፡፡

፲፰. የመንግስት ሠራተኛ የነበረ ጠበቃ
. ማንኛውም ከዚህ ቀደም የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ባለሥልጣን የነበረ ጠበቃ በቀጥታ በወሰነባቸው ወይም በጥልቀት በተሳተፈባቸው ጉዳዮች ላይ ከቀድሞ አሠሪው ጋር ተመካክሮ የጽሑፍ ፈቃድ ካልተሰጠው መስተቀር ለአንድ ደንበኛ የሙያ አገልግሎ መስጠት አይችልም፡፡
. ሕግ በግልጽ ካልፈቀደ በስተቀር የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ባለሥልጣን በነበረበት ጊዜ አንድን ግለሰብ በተመለከተ መረጃ ያገኘ ጠበቃ መረጃው ከሚመለከተው ሰው ጥቅም ጋር የሚፃረር ጥቅም ላለው ሰው የጥብቅና አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም፡፡

፲፱. ዳኛ ወይም የሽምግልና ዳኛ ወይም አስታራቂ
. ማንኛውም ጠበቃ ቀደም ሲል በዳኝነት ወይም አንድን ወገን በመወከል ሳይሆን በገለልተኝነት በሸምግልና ዳኝነት የተካፈለበትን ወይም በአስታራቂነት ወይም በሕግ ጉዳይ ፀሐፊነት የተሳተፈበት ጉዳይ በሚመለሰከት በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን የጥብቅና አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ በዳኝነት በሽምግልና ዳኝነት በአስታራቂነት በሕግ ጉዳይ ፀሐፊነት ወይም በተመሳሳይ ኃላፊነት በሚሠራበት ወቅት በዚሁ ጉዳይ ተካፋይ የሆነ ባለጉዳይ ወይም የሕግ ባለሙያ በሠራተኛነት እንዲቀጥረው ሊደራደር አይችልም፡፡
. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () የተከለከለ ጠበቃ አባል የሆነበት የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ጠበቃው አገልግሎት እንዳይሰጥ በተከለከለበት ጉዳይ ላይ በሌላ ጠበቃ አማካኝነት አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለው፤
) የተከለከለው ጠበቃ በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት ተሳትፎና ከአገልግሎት ክፍያውም ድርሻ እንዳይኖረው ከተደረገ
) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () ለተመለከተው ጉዳዩን ላየው አካል ይህ ደንብ አለመጣሱ እንዲያረጋግጥ ይደረግ ዘንድ ተገቢው የጽሑፍ ማስታወሻ በወቅቱ የተላከበት ከሆነ፡፡

. የአስታራቂነት ሥራ መሥራት
. ማንኛውም ጠበቃ ከዚህ የሚከተሉትን ድንጋጌዎች በመከተል በሁለት ደንበኞች መካከል በአስታራቂነት ሊሠራ ይችላል፡፡
) ጠበቃው ሁለት ደንበኞችን ለማስታረቅ መሥራቱ የሚኖረውን እንድምታ ጥቅምና ጉዳቱን ጨምሮ ካስረዳቸው በኋላ ሁለቱም ደንበኞች በጠበቃው አስታራቂነት የተስማሙ ሲሆን፤
) በጠበቃው ሚዛናዊ ግምት ጉዳዩ ከሁለቱ ወገኖች ጥቅም ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ይፈታል ብሎ ሲያምን በተለይም እያንዳንዱ ደንበኛ በጉዳዩ ላይ አጥጋቢ ውሣኔ ለመስጠት ይችላል ብሎ ሲገምት፤
) ጉዳዩ በእርቅ ሳይፈታ ቢቀር በየትኛውም ወገን ጥቅም ላይ መሠረታዊ የሆነ ጉዳት ይደርሳል ተብሎ የማይጠበቅ ሲሆን እና
) ሁለቱን ደንበኞቹን በጋራ የመወከሉን ኃላፊነት በገለልተኝነት ለመወጣት የሚችልና የትኛውም ወገን ላይ ተገቢ ያልሆነ ተጽዕኖ የማያሳድር መሆኑን ሲያረጋግጥ፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ የአስታራቂነት አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ ከእያንዳንዱ ደንበኛ ጋር የሚደረስበትን ውሣኔ በመመካከር እና በጉዳዩ ላይ ውሣኔ ለመስጠት የሚረዱትን ቁም ነገሮች በሙሉ እንዲገነዘቡ በማድረግ እያንዳንዱ ደንበኛ የተሟላና አጥጋቢ ውሳኔ እንዲሰጥ መርዳት አለበት፡፤
. ማንኛውም ጠበቃ ከደንበኞቹ አንዱ አስታራቂነት አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ በጠየቀ ጊዜ ወይም በንዑስ አንቀጽ() ከተመለከቱቱ ሁኔታዎች አንዱን መሟላት ባልቻለ ጊዜ የአስታራቂነት አገልግሎቱን ያቋርጣል:: ከአቋረጠም በኋላ በዚያው ጉዳይ ላይ ለማንኛውም ወገን የጥብቅና አገልግሎት ለመስጠት አይችልም፡፡

፳፩. ለድርጅት ጠበቃ ስለመሆን
. ለአንድ ድርጅት የጠበቃ አገልግሎት የሚሰጠው በድርጅቱ ደንብ መሠረት አግባብ ያላቸውን የድርጅቱን የሥራ ኃላፊዎች እያማከረ ይሆናል፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ የድርጅቱ ተወካይ ሆኖ በሚሠራበት ወቅት የድርጅቱ ባለሥልጣን ተቀጣሪ ወይም ከድርጅቱ ጋር ተባባሪ ሆኖም የሚሠራ ሌላ ሰው ድርጅቱን በሕገ ወጥነት ሊያስጠይቅ በሚችል ሁኔታ አንድን ድርጊት በመፈፀም ወይም ባለመፈጸም በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ብሎ በገመተ ጊዜ ጉዳቱን ለመከላከል ይቻል ዘንድ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ በጠበቃው ሊወሰዱ ከሚችሉ እርምጃዎች የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
) ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ መጠየቅ
) በጉዳዩ ላይ የተለየ አስተያየት ቀርቦበት ሥልጣን ላለው የድርጅቱ አካል እንዲቀርብ ምክር መስጠት ወይም
) ጉዳዩን ከፍ ላለው የድርጅቱ አካል ማቅረብ ወይም ጉዳዩ አሳሳቢና ከባድ በሆነ ጊዜ ደግሞ ለድርጅቱ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጭ አካል ማቅረብ፡፡
. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () በተመለከተው መሠረት ተገቢው ውሣኔ እንዲሰጥበት አስፈላጊው ጥረት ተደርጎ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጭው አካል ሕግን የሚጥሰውና በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል የሚችለው እርምጃ እንዲቀጥል ከወሰነ ጠበቃው አገልግሎቱን በፈቃዱ መልቀቅ ይጠበቅበታል፡፡
. ጠበቃው የድርጅቱን መሪ ባለሥልጣን ሠራተኛ ባለአክሲዮን ወይም በድርጅቱ የታቀፈ ሰው ጉዳይ በሚያይበት ጊዜ የእነዚህ ሰዎች ጥቅም ከድርጅቱ ጥቅም ጋር የሚጋጭ መሆኑ ከታወቀ የሰውዬውን ማንነት ማስረዳት አለበት፡፡
. የጥቅም ግጭትን በተመለከተ የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው አንድን ድርጅት ወክሎ የሚሠራ ጠበቃ የድርጅቱን መሪዎች ባለሥልጣኖች ሠራተኞች ባለአክሲዮኖች ወይም ሌሎች ሰዎችን በመወከል ሊሰራ ይችላል፡፡

፳፪. ችሎታ ለሌለው ሰው ጠበቃ ስለመሆን
. ደንበኛው ለአካለ መጠን ባለመድረሱ የአእምሮ መታወክ የገጠመው በመሆኑ ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት ከውክልናው ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት ባልቻለ ጊዜ ጠበቃው የጠበቃና የደንበኛን መደበኛ ግንኙነት በመጠበቅ መሥራት አለበት፡፡
.ጠበቃው ደንበኛው የራሱን ጥቅም በአግባቡ ለማስጠበቅ የማይችል መሆኑን በተረዳ ጊዜ ሞግዚት እንዲመደብለት ማድረግ ወይም ጥቅሙን ለማስጠበቅ የሚረዱ ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ ይኖርበታል፡፡

፳፫. የሕግ ሙያ ያልሆኑ ተደራቢ ሥራዎች
. ማንኛውም ጠበቃ በሕግ ሙያ አገልግሎት በተሰማራበት ወቅት ተደራቢ የንግድ ወይም ሌላ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ሥራ የሚያከናውን በሆነ ጊዜ በተደራራቢነት የሚሠራው ሥራ የሙያውን ታማንነት ነፃነት ብቃትና ክብር እንዳይቀንሰው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ከሙያው ውጭ የሚያከናውነውን ተደራቢ ሥራውንና የተሳትፎውን መጠን ለደንበኛው የማስታወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ከሙያው ውጭ የሆነ ተደራቢ ሥራ በሚሠራበት ወቅት ከደንበኞቹ ጋር የሚያደርገው ግንኙነት ከጥብቅና ሙያው ውጭ መሆኑን በግልጽ እንዲረዱለት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ከጥብቅና ሙያው ውጭ በሆነ ሥራ ተሰማርቶ የሚያገኘውን ገቢ በጥብቅና ሙያው ካገኘው ገቢ ለይቶ የሚያሳይ የሂሣብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡

፳፬. የደንበኛን ንብረት ስለመጠበቅ
. ማንኛውም ጠበቃ ከውክልናው ጋር በተያያዘ የደንበኛን ንብረት በአደራ በሚጠብቅበት ወይም በሚያስተዳድርበት ጊዜ በኢትዮጵያ ሕግ የታዘዙትን የጥንቃቄ እርምጃዎች በሙሉ የማክበር አግባብነት ያለው ሕግ በሌለ ጊዜ ደግሞ ጠንቃቃ ባለንብረት የሚወስዳቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ደንበኛው በስሙ ንብረት የሚረከብ መሆኑን በግልጽ የሚያውቅ ካልሆነ በስተቀር የደንበኛውን ንብረት እንደተረከበ መረከቡን የማስታወቅ ግዴታ አለበት፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ የደንበኛውን ንብረት በአደራ በሚጠብቅበት ወይም በሚያስተዳድርበት ወቅት ንብረቱን ለመተሳሰብና ለባለመብቱ ለማስረከብ በሚያመች ሁኔታ መዝግቦ የመያዝ ግዴታ አለበት፡፡  በባንክ መቀመጥ ያለበት ገንዘብ ካለም ለብቻው የተለየ የባንክ ሂሳብ መክፈት አለበት፡፡
. ጠበቃው የያዛቸው ንብረትና መረጃዎች ለማየት ሥልጣን የሌላቸው ሰዎች እንዳይመረምሩት ተገቢውን ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ደንበኛው ንብረቱን ለመረከብ በጠየቀ ጊዜ ወይም ንብረቱን ለባለመብቱ ማስረከብ ተገቢ በሆነ ጊዜ የማስረከብ ኃላፊነት አለበት፡፡
. ጠበቃው የደንበኛው ንብረት ባለአደራና አስተዳዳሪ በሆነበት ጊዜ በሦስተኛ ወገኖች የተያዘን ንብረት የማስመለስ የደንበኛውን የባለንብረትነት ማረጋገጫ መዛግብትና ሌሎች መረጃዎች የማየት መብት አለው፡፡

፳፭. የደንበኛን ልዩ ፈቃድ ስለማግኘት
ጠበቃ ለደንበኛው በሕግ የተፈቀደለትን የይርጋና ሌሎች ተመሣሣይ መብቶችን በታቃውሞነት በክርክር ወቅት ላያቀርብ የሚችለው ሁኔታውን ለደንበኛው ካስረዳ በኋላ ደንበኛው በጽሑፍ ከፈቀደለት ብቻ ነው፡፡

፳ጜ. ጉዳዩ በስምምነት እንዲያልቅ ስለመገፋፋት
ጠበቃው የደንበኛው ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ ከሚወሰን ይልቅ በእርቅ ቢያልቅ ተገቢውን ውጤት የሚያስገኝ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ጉዳዩ በእርቅ እንዲያልቅ ሊገፋፋ ይችላል፡፤

፳፯. የተከላካይ ጠበቃ ኃላፊነት
. ማንኛውም ተከላካይ ጠበቃ በደንበኛው ላይ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት የጥፋተኛነት ውሳኔ ሊያሰጥ የሚያበቃ በቂ ማስረጃ መቅረቡን ካላረጋገጠ በስተቀር ደንበኛው በጥፋተኛነት እነዳይቀጣ የመከራከር ግዴታ አለበት፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ደንበኛው በተከሰሰበት ወንጀል ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ መሆኑን ማወቁ ወይም በማስረጃነት የሚያቀርባቸው ነገሮች የማያዋጡ መሆናቸውን ማወቁ ለደንበኛው ተገቢውን የክርክር አገልግሎት እንዳይሰጥ ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችል በመግለጽ ደንበኛውን አስቀድሞ ማስጠንቀቅ ይጠበቅበታል፡፡
. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () ድንጋጌ የወንጀል ተከሳሽ በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ከመባሉ በፊት እያንዳንዱን የጉዳዩን ነጥብ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ጠበቃው የሚያደርገውን ማጣራትና ክርክር አይመለከትም፡፡

፳፰. አከራካሪ ጉዳይ በሌለበት ክስና ክርክር ስለአለማቅረብ
ማንኛውም ጠበቃ ተከራካሪን ለማጉላላት ክስ ማቅረብና መከራከር በተለይም አከራካሪ የሆነ ጭብጥ በሌለበትና የክርክሩ ውጤት በተከራካሪ ወገኖች መብት ላይ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑ በግልጽ በሚታይበት ጉዳይ ክስ ማቅረብና መከራከር አይችልም፡፡

፳፱. ለተቃራኒ ወገን ቅን ስለመሆን
ማንኛውም ጠበቃ የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም የለበትም
. ተቃራኒ ወገን ማስረጃ እንዳያገኝ ማናቸውም እንቅፋት መፍጠር ወይም ሌሎች ሰዎች ይህን መሰል አድራጎት እንዲፈጽሙ መምከር ወይም መርዳት፤
. ማስረጃን ማሳሳት ወይም ሌሎች ሰዎች ይህን መሰል አድራጎት እንዲፈጽሙ መምከር ወይም መርዳት፤
. ከጉዳዩ ጋር ግንኑኝነት የሌለው ወይም በማስረጃ ሊደገፍ የማይቸችል ነገር ማቅረብ በምስክርነት ካልቀረበ በስተቀር በግሉ የሚያውቀውን የጭብጥ ፍሬ ነገሮች መሰንዘር ወይም የጉዳዩን ፍትሃዊነት የአንድን ምስክር ተአማኒነት የተከሳሽን ጥፋተኛ ወይም ተጠያቂ መሆንና አለመሆን አስመልክቶ የግል አስተያየቱን መስጠት
. ደንበኛው ወይም ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ የማይገደዱ ሰዎችን በመተመለከተ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ማንኛውንም ሰው ለተቃራኒ ወገን የምስክርነት ቃሉን ወይም ሌላ አግባብነት ያለው መረጃ እንዳይሰጥ መገፋፋት፡፡

. በጠበቃ ያልወከለ ተከራካሪ ሲያጋጥሞ
ማንኛውም ጠበቃ ጠበቃ ያልወከለ ተከራካሪ ባጋጠመው ጊዜ ጠበቃው ሆን ብሎ ይህንኑ ተከራካሪ ወገን ሊያሳስቱ የሚችሉ ድርጊቶች ከመፈጸም መቆጠብ አለበት፡፡ ከታቻለም ጠበቃ ላልያዘው ተከራካሪ ጉዳዩን በተመለከተ የጠበቃ ሚና ምን እንደሆነ ማስረዳት አለበት፡፡

፴፩.የሦስተኛ ወገኖችን መብት ስለማክበር
ማንኛውም ጠበቃ ለደንበኛው በሚሰጠው የጥብቅና አገልግሎት ሦስተኛ ወገኖችን ማጉላላት ማዋረድ ወይም በእነዚሁ ወገኖች ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና መፍጠር ሌላ መሠረታዊ ግብ በሌለው ወይም የሦስተኛ ወገኖችን ሕጋዊ መብት በሚገፋ መንገድ ማስረጃ የማግኘት ዘዴ መጠቀም የለበትም፡፡

፴፪. ጉዳዩን በመገናኛ ብዙሃን ስለመግለጽ
. ማንኛው ጠበቃ በሕግ ሙያ አገልግሎቱ ምክንያት ያወቀውን መረጃ ለመገናኛ ብዙሃን ሊገልጽ የሚችለው በሚዛናዊ የህሊና ግምት የመረጃው መገለጽ የፍርድ ሂደትን የሚያደናቅፍና የደንበኛውን ጥቅም የማይጎዳ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
. በንዑስ ቁጥር () የተመለከተው ክልከላ ቢኖርም ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ ሳይገባ ጠበቃው በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን መረጃ ለመስጠት ይችላል፤
/ የክሱን ወይም የመከላከያውን ጠቅላላ ሁኔታ ወይም ዓይነት እንዲሁም የወንጀል ጉዳይ ከሆነ የክሱን ዓይነት በሕግ ካልተከለከለ በስተቀር የወንጀል ክሱን ወይም የመከላከያውን ዓይነት ጉዳዩ የሚመለከታቸውነ ሰዎች ማንነት፡፡
/ በሕዝብ መዝገብ ውስጥ የሰፈረን መረጃ
/በጉዳዩ ላይ የተሰጠውን ቀነ ቀጠሮ ወይም ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ
/ መረጃ ለመሰብሰብ የቀረበን የዕርዳታ ጥያቄና የተፈላጊውን መረጃ ዓይነት
/ ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው በግለሰቦች ወይም በሕዝብ ላይ ከፍተና አደጋ ሊያስከትል ይችላል የሚል ግምት ካለ ስለዚሁ ሰው ባህርይ አደገኛነት ማስጠንቀቂያ
. ጠበቃ በደንበኛው ላይ የተሰራጩትን አሉታዊ ዜናዎችና መግለጫዎች በማስተባበል የደንበኛውን ጥቅምና መልካም ስም ለማስጠበቅ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሚዛናዊ የሆነ የማስተባበያ ወይም የማለዘቢያ መግለጫ ለመገናኛ ብዙሃን ለመስጠት ይችላል፡፡

፴፫. የጥብቅና አገልግሎት ስለማቋረጥ
. ማንኛውም ጠበቃ ለደንበኛው ሊሰጥ የገባውን የጥብቅና አገልግሎ ውል ለማቋረጥ የሚያስችል በቂና አሳማኝ ምክንያት ከሌለው በስተቀር በገባው ውል ግዴታ መሠረት የደንበኛውን ጉዳይ እስከ መጨረሻው የመከታል ግዴታ አለበት፡፡
. ጠበቃው ለደንበኛው በገባው የውል ግዴታ መሠረት የደንበኛውን ጉይይ እስከ መጨረሻው ለመከታተል ባልቻለ ጊዜ ሁኔታውን ለደንበኛው የመግለጽና አገልግሎቱን በማቋረጡ ምክንያት በደንበኛው ላይ ሊደርስ የሚችለውን ወጭና መጉላላት ለመቀነስ እንዲሁም ጉዳዩ በተቃና ሁኔታ በሌላ ጠበቃ ሊሸፈን የሚችልበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት፡፡

፴፬. አገልግሎት ለማቋረጥ በቂ ምክንያቶች
ጠበቃ ለደንበኛው የሚሰጠውን አገልግሎ ለማቋረጥ የሚያስገድዱ በቂ ምክንያቶች የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡
. ይህን የሥነ ምግባር ደንብ ወይም ሌላ ሕግ የሚጥስ ከሆነ
. ጠበቃው የተወከለበት ጉዳይ በመታየት ላይ ባለበት ወቅት ደንበኛው በጉዳዩ አካሄድ ላይ አስነዋሪ እርምጃ የወሰደ ከሆነና ከጠበቃው የሚያገኘውን አገልግሎ ለወንጀል ወይም ለማታለል ድርጊት ከተጠቀመበት ወይም ክርክሩን በሌላ ሰው ላይ መጉላላት ለማስከተል ወይም ጉዳት ለማድረስ የተጠቀመበት ከሆነ
. ጠበቃው ጉዳዩን በአግባቡ ለመምራት ችሎታና ብቃት ያነሰው እንደሆነ ወይም ከጥብቅና ሥራው ከተወገደ
.ደንበኛው ውክልናውን በተመለከተ ከጠበቃው የሚፈለግበትን ግዴታ ሳይወጣ ሲቀር እና ግዴታውን ካልፈጸመ አገልግሎ የሚያቋረጥ መሆኑን ጠበቃው ካስጠነቀቀው
. በጠበቃውና በደንበኛው መካክል ሊኖር የሚገባው መተማመን አንዱ ወገን የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸሙ የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ የተናጋ ከሆነ
. የጉዳዩን ሂደት በሚመለከት ጠበቃው ወሣኝ በሆኑ ነገሮች ላይ የሚሰጠውን የሕግ ምክር ደንበኛው ውድቅ በማድረጉ የተነሣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ሊኖር የሚገባው መተማመን ከጠፋ
. ደንበኛው ለጠበቃው መክፈል ያለበትን የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍልና ሌሎችም ወጭዎች እንዲተካ ተገቢው ማሳሳቢያ ተሰጥቶት ኃላፊነቱን ለመወጣት ፈቃደኛ አለመሆኑን በግልጽ ካሳየ::

፴፭. አገልግሎ የሚያቋርጥ ጠበቃ ግዴታዎች
ማንኛወም ጠበቃ ውል ሲያቋርጥ የሚከተሉትን ግዴታዎች መወጣት አለበት፡፡
. ለደንበኛው በቂ ማስታወቂያ መስጠት እና ደንበኛው ሌላ ጠበቃ እንዲወክል በቂ ጊዜ መስጠት
. የደንበኛውን ንብረትና ሠነዶች ሥርዓት ባለው መንገድ ወዲያውኑ ማስረከብ
. ስለጉዳዩ ደንበኛው የሚጠይቀውን ማንኛውንም መረጃ መስጠት
. በደንበኛው እጅ የሚገኝ ማንኛውንም ሂሣብ መተሳሰብ ወደፊት ለሚሠራ ሥራ የተቀበለውን ገንዘብ ከውጪ ቀሪውን ተመላሽ ማድረግ
.ለሥራ ማስኬጃ የተረከባቸውን ሂሳቦች መተሳሰብና ከወጪ ቀሪ መመለስ
. ከተተኪው ጠበቃ ጋር በመተባበር በጉዳዩ መጓተት መቋረጥ ወይም አላስፈላጊ ወጭ እንዳያጋጥመው መከላከል፡፡

፴ጜ. የተተኪ ጠበቃ ግዴታዎች
. ተተኪው ጠበቃ ደንበኛው ከቀድሞ ጠበቃው ጋር ያለውን ማንኛውንም ሂሣብ እንዲያወራርድ ማስገንዘብ ይጠበቅበታል፡፤
. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ () የተመለከተው ደንበኛው ለቀድሞ ጠበቃው መክፈል ያለበትን የአገልግሎት ክፍያ አለማጠናቀቁ አዲሱ ጠበቃ በቀጠሮ ቀን በፍርድ ቤት ተገኝቶ ተገቢውን አገልግሎት እንዳይሰጥ ሊያግደው አይችልም፡፡

፴፯. በሸሪክ ወይም በተቆጣጣሪ ጠበቃ ስለሚሰጥ የጥብቅና አገልግሎ
. የጥብቅና ድርጅት ሸሪክ የሆነ ጠበቃ በድርጅቱ ውስጥ የሚሠራ ማንኛውም የሕግ ባለሙያ ይህን የሥነ ምግባር ድንብ ማክበሩን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡
. ማንኛወም ሌላውን ጠበቃ በቀጥታ የመቆጣጠር ሥልጣን ያለው ጠበቃ በእርሱ ሥር የሚያገለግል ጠበቃ የሙያውን የሥነ ምግባር ደንብ ማክበሩን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ለሌላ ጠበቃ የሥነ ምግባር ጉድለት ተጠያቂ የሚሆነው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው
/ ጥፋት የፈጸመው ሰው ድርጊቱን የፈጸመው በጠበቃው ታዝዞ ሲሆን ወይም ጉድለት እየተፈጸመ መሆኑን እያወቀ ድርጊቱን ያፀደቀው ሲሆን
/ ጥፋት የፈጸመው ሰው ጠበቃው በሚሠራበት የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ሸሪክ ከሆነ ወይም በጠበቃው ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥራ የሚሠራ ከሆነና ግለሰቡ በሥነ ምግባር ደንብ የሚያስቀጣ ድርጊት እየፈጸመ መሆኑን እያወቀ ድርጊቱ የሚያስከትለውን የማስተካከያ እርምጃ ያልወሰደ ሲሆን፡፡

፴፰. ክልከላ
. በማንኛውም የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ውስጥ የሚሠራ ጠበቃ በድርጅቱ ውስጥ ከሚሠሩት ሌሎች ጠበቃዎች አንዱ በዚህ ደንብ መሥረት አንድን ጉዳይ በጥብቅና ለብቻው ከመያዝ የሚያግደው ምክንያት መኖሩን እያወቀ የጥብቅና አገልግሎ ለመስጠት አይችልም፡፡
. የሚከተሉት ሁኔታዎች ካላጋጠሙ በስተቀር የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት የለቀቀ በድርጅቱ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ወክሎት የነበረ ደንበኛ ጥቅም ጋር የሚጋጭ ጥቅም ያለው ደንበኛን ድርጅቱ ከመወከል አያግደውም፡፡
/ ጉዳዪ ከዚህ ቀደም ለድርጅቱ የቀረበ ወይም ከቀድሞው ጉዳይ ጋር መሠረታዊ በሆነ መንገድ የተያያዘ ከሆነ
/ በጥብቅና አገልግሎ ሰጭ ድርጅት ውስጥ ያለ ጠበቃ በቀረው ጉዳይ ላይ በማስረጃነት ሊያገለግል የሚችል መረጃ በእጁ የሚገኝ ከሆነ
. በዚህ አንቀጽ የተጣለው ክልከላ ጉዳዩ የሚመለከተው ደንበኛ ክልከላው ተፈጸሚ እነዳይሆን በጽሑፍ በተስማማ ጊዜ ቀሪ ይሆናል፡፡

፴፱. የበታች ጠበቃ ግዴታ
. በሌላ ጠበቃ አመራር ሥር የሚሠራ ማንኛውም ጠበቃ ይህን የሥነ ምግባር ደንብ ማክበር አለበት፡፡
.የበታች ጠበቃ አከራካሪ በሆነ የሥነ ምግባር ጥያቄ ላይ የበላዩን ትዕዛዝ በመቀበል የሠራ መሆኑን ለማስረዳት በቻለ ጊዜ ከተጠቃቂነት ነፃ ይሆናል፡፡

. የሕግ ሙያተኛ ያልሆኑ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን ስለመቆጣጠር
የሕግ ባለሙያ ያልሆነን ሰው በተቀጣሪነት ወይም ለሚሰጠው አገልግሎት የተወሰነ ክፍያ በመስጠት ወይም በተባባሪነት የሚያሠራ ጠበቃ ወይም ጥብቅና አገልግሎት ድረጅት፤
. ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃና ተፈላጊውን ቁጥጥር በማድረግ የግለሰቡ ምግባር ይህን የሥነ ምግባር ደንብ እነዳይጥስ ይቆጣጠራል፡፡
. የሕግ ሙያተኛ ያልሆነው ባልደረባ ለፈጸመው የሥነ ምግባር ጉድለት ጠበቃው ተጠያቂ የሚሆነው
/ድርጊቱን እንዲፈጽም ያዘዘው ከሆነ ወይም የተፈጸመውን ድርጊት የሚያውቅ ከሆነና አፈጻጸሙንም የፈቃደ ወይም ያጸደቀ ከሆነ
/ሙያተኛ ባልሆነው ሰው ላይ የቁጥጥር ሥልጣን ኖሮት የሥነ ምግባር ጉድለት የሆነውን ድርጊት መፈጸሙን እያወቀና ድርጊቱ የሚያስከትለውን ውጤት ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ እየቻለ ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ያልወሰደ ከሆነ ነው፡፡

፵፩. ሙያዊ ነፃነት
. ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት በሚከተሉት ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር የጥብቅና አገልግሎት ክፍያን ጠበቃ ካልሆነ ሰው ጋር መካፈል አይችልም
/ ጠበቃው ከጥብቅና ድርጅቱ ከሸሪኩ ወይም ተባባሪው ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሠረት በሚሞትበት ጊዜ ወደ ሟቹ ጠበቃ ሀብት ወይም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለይቶ ላስታወቃቸው ሰዎች የሚደረግ ክፍያ
/ ከሟች ችሎታ ካጣ ወይም ከጠፋ ጠበቃ ላይ የጥብቅና አገልግሎ ድርጅት የገዛ ሰው ለሟች ጠበቃ ሀብት ወይም ለተወካዩ የሚፈጽመው የግዥ ክፍያ
/ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የሕግ ባለሙያ ላልሆኑ ሠራተኞች የአገልግሎ ወይም የጡረታ ዋስትና ተጠቃሚ ከሚያደርገው ስምምነት ውስጥ በመግባቱ የሚደረግ ክፍያ፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ የሕግ ሙያተኛ ካልሆነ ሰው ጋር የጥብቅና አገልግሎትን የሚያካትት የሽርክና ግንኙነት መመሥረት ወይም ሙያዊ ግዴታውን በመወጣት ረገድ የሕግ ሙያተኛ ላልሆነ ሰው የመምራትና የመቆጣጠር ሥልጣን በሚሰጥ ሁኔታ መሥራት አይችልም፡፡

፵፪. የአገልግሎ ክፍያ አተማመን
ማንኛውም ጠበቃ ከደንበኛው የሚጠይቀው የአገልግሎት ክፍያ ተገቢና ሚዛናዊ መሆን አለበት፡፡ የክፍያውን መጠን ለመወሰን የሚከተሉትን መመዘኛዎች ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡
. ለደንበኛው የሚሰጠው አገልግሎት የሚወስደው ጊዜና የሚጠይቀው ድካም
.ጉዳዩን በሚገባ ለማከናወን የሚያስፈልገው ችሎታ የጉዳዩ አዲስነት እና አስቸጋሪነት
.ከደንበኛው ጋር የሚደረገው የጥብቅና ሥራ ስምምነት የሌሎች ደንበኞችን ጉዳይ ተቀብሎ ለመሥራት የሚያስችል መሆን አለመሆኑን
. ተመሣሣይ ጉዳዮች በተለምዶ የሚያስከፍሉትን የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ መጠን
. ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የሀብት ግምት እና የሚገኘው ውጤት
. በጠበቃውና በደንበኛው መካከል ያለው የሙያ ግንኙነት ርዝመት እና
. የጠበቃው የሥራ ልምድ ጥሩ ዝናና የሙያ ችሎታ እና
.ሌሎች መሰል መመዘኛዎች

፵፫. የአገልግሎት ክፍያ ስምምነት
. የአገልግሎ ክፍያ ስምምነት በጽሑፍ የሚደረግና በተዋዋይ ወገኖች ወይም በወኪሎቻቸው የሚፈረም ሕጋዊ ሰነድ ነው፡፡
.በጠበቃና በደንበኛ መካከል የሚፈፀም የአገልግሎት ክፍያ ስምምነት የሚከተሉትን መሠረታዊ ጉዳዮች ይወስናል
) ደንበኛው ለጠበቃው የሚከፍለውን አጠቃላይ ገንዘብ ደመወዝ የማካካሻ ክፍያ የመጠባበቂያ ክፍያ ወይም ሌላ ክፍያ ሥርዓት በመግለጽ የአከፋፈሉን ስልትና ጊዜ
/ ጠበቃው በጉዳዩ ላይ የሚያስገኘውን የውጤት ዓይነት ወይም ዓይነቶች››

፵፬. መጠኑ ያልተወሰነ የአገልግሎት ክፍያ ስምምነት
የአገልግሎት ክፍያው ክርክሩ በሚያስገኘው የገንዘብ መጠን ላይ የተመሠረተ በሆነ ጊዜ ስምምነቱ የሚከተሉትን መሠረታዊ ጉዳዮች የያዘ ይሆናል፡፡
.ጉዳዩ በስምምነት፡በይግባኝ ወይም በሌላ መንገድ ቢያልቅ ከእነዚህ ሁኔታዎች ባንዱ ደንበኛው ከሚያገኘው ገንዘብ ላይ ለጠበቃው በመቶኛ ስሌት ሊከፈለው የሚገባውን የገንዘብ መጠን፡
. ለጠበቃው የሚደርሰው ሂሳብ የዳኝነት ክፍያ እና ሌሎች ወጭዎች ከተቀናነሱ በኋላ የዳኝነት ክፍያ እና ሌሎች ወጭዎች ከተቀናነሱ በኋላ የሚታሰብ ወይም ከአጠቃላዩ ገንዘብ ሚታሰብ መሆኑን፡፡

፴፭. መጠኑ ያልተወሰነ የአገልግሎት ክፍያ የማይጠየቅባቸው ጉዳዮች
ጠበቃ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ያልተወሰነ የአገልግት ክፍያ ስምምነት ሊያደርግ አይችልም
. በመደበኛ ፍርድቤተ በባልና ሚስት ክርክር ፍቺን በማስገኘት ላይ ተመስርቶ ወይም በሚያስወስነው የቀለብ ወይም የልጆች ማሳደጊያ ገንዘብ ወይም በሚያስገኘው የንብረት መጠን፡፡
. በወንጀል በተከሰሰ ሰው ላይ ፍርድ ቤት በሚሰጠው ውሳኔና ቅጣት ላይ ተመርኩዞ፡፡

፵ጜ. በደንበኞች መካከል የጥብቅና አገልግት ክፍያን በድርሻቸው ስለማከፋፈል
በአንድ ጉዳይ ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች ወክሎ የሚከራከር ጠበቃ በተቃራኒው ግልጽ የሆነ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የአገልግሎ ክፍያውን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እያንዳንዱ ደንበኛ ድርሻውን እንዲከፍል ያደርጋል፡፡

፵፯. የአገልግሎት ክፍያን ከሌላ ጠበቃ ጋር ስለመካፈል
ማንኛውም ጠበቃ የአገልግሎት ክፍያን የሙያ ሸሪኩ ካልሆነ ሌላ ጠበቃ ጋር ለመካፈል የሚችለው፡
. ሌላው ጠበቃ በጉዳዩ ላይ አገልግሎት እንዲሰጥ ደንበኛው ቀጥተኛ በሆነ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የፈቀደ ሲሆን እና
.የገንዘብ አከፋፈሉ እያንዳንዱ ጠበቃ ከሠራው ሥራና ከተቀበለው ኃላፊነት ጋር ተመጣጣኝ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

፵፰. የሕግ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች አባል ስለመሆን
ማንኛውም ጠበቃ የጥብቅና አገልግሎ ሰጪ ድርጅቶች አባል ለመሆ ይችላል፡፡ ጠበቃው አባል የሆበት ድርጅት በሚሰጣቸው ውሣኔዎች ወይም በሚወስዳቸው እርምጃዎች ላይ መካፈል የማይችለው፡፡
. በውሣኔው የሚሰጠው ሰው ወይም ማህበረሰብ ከጠበቃው ወይም ከጠበቃው ደንበኛ ጋር የማይጣጣም ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው ሲሆን
. አገልግሎት የሚሰጠው ሰው ወይም ማህበረሰብ ከጠበቃው ወይም ከጠበቃው ደንበኛ ጋር የማይጣጣም ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው ሲሆን

፵፱. ነፃ የሕግ አገልግሎት ስለመስጠት
ማንኛውም ጠበቃ በነፃ ወይም በአነስተኛ ክፍያ በዓመት ቢያንስ የ፶ ሰዓት የሕግ አገልግሎ መስጠት አለበት፡፡ አገልግሎት የሚሰጠውም
.የመክፈል አቅም ለሌላቸው ሰዎች
.ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለሲቪክ ድርጅቶች ለማህበረሰብ ተቋማት
.ፍርድ ቤት የጥብቅና አገልግሎ እንዲገኙ ለሚጠይቃቸው ሰዎች
. ሕግን የሕግ ሙያንና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ለሚሠሩ ኮሚቴዎችና ድርጅቶች ነው፡፡

. አገልግሎትን አስመልክቶ ስለሚሰጥ መግለጫ
ማንኛውም ጠበቃ ስለ እራሱ ወይም ስለሚሰጠው አገልግሎ ሀሰተኛ ወይም የሚያሳስት መግለጫ መስጠት የለበትም፡፡ ከጠበቃ የሚሰጥ መግለጫ ሀሰተኛ ወይም የሚያሳስትም ነው ሊባል የሚችለው
. ፍሬ ነገር ወይም ሕግ ያልሆነውን እንደሆነ አድርጎ ላቀረበ ወይም አንድን ፍሬ ነገር በመደበቅ አንድን አባባል እውነት አስመስሎ ካቀረበ
. ጠበቃ በክርክር ሊያስገኘው የሚችለውን ውጤት ከገፋፋ ወይም ይህን የሥነ ምግባር ደንብ የሚጥስ ዘዴን በመጠቀም ለጉዳዩ ውጤት ለማስገኘት ቃል የገባ ሲሆን
. በተጨባጭ ማረጋገጥ የሚቻል ካልሆነ በስተቀር አንድ ጠበቃ የራሱን የጥብቅና አገልግሎት ከሌሎች ጠበቆች አገልግሎት ጋር በማነፃፀር የራሱን አጉልቶ የሚያሳይ መግለጫ ከሰጠ ነው

፶፩. ደንበኛን አስመልክቶ ስለሚሰጥ መግለጫ
ማንኛውም ጠበቃ የደንበኛውን ጉዳይ አስመልክቶ በሚለጠፍ ማስታወቂያና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ዘዴዎች ማስታዋወቅ ይችላል፡፡ ማስታወቂያው አጭር ግልጽና ትክክለኛ ሆኖ የጠበቃውን ስም አድራሻ የሚሰጠውን አገልግሎና የሥራ ልምድ መግለጽ ይኖርበታል፡፡
ማንኛውም ጠበቃ ማስታወቂያውን ለመገናኛ ብዙሃን ከመላኩ ከሠላሳ ቀናት በፊት ለጥብቅና ፈቃድ ሰጭው አካል አንድ ኮፒ እንዲደርሰው ማድረግ አለበት፡፡
በዚህ አንቀጽ መሠረት ለሚዘጋጅ ማስታወቂያ ይዘት ተጠያቂ የሚሆን ቢያንስ የአንድ ጠበቃ ስም መጨመር አለበት፡፡

፶፫. የሙያ ዘርፍን ስማስተዋወቅ
. ማንኛውም ጠበቃ በተወሰነ የሕግ ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጥ ወይም የማይሰጥ መሆኑን ማስታወቅ ይችላል፡፡
. ጠበቃ በተወሰነ የሕግ ዘርፍ ልዩ ዕውቀት ወይም የጠበብትነት አለኝ ብሎ ለማስታወቅ የሚችለው የልዩ ዕውቀት ወይም የጠበብትነት ማዕረግ ለመስጠት በሕግ ሥልጣን የተሰጠው አካል የምስክር ወረቀት ሲሰጠውና ምስክርንቱ በጥብቅና ፈቃድ ሰጪው አካል ሲታወቅ ነው፡፡

፶፬. በድርጅት ስም ስለመጠቀም
.ማንኛውም ጠበቃ የሚጠቀምበት የጥብቅና አገልግሎት ድርጅት ስያሜ ከመንግሥት ከሕዝብ ወይም ከበጎ አድራጎት ድርጅት ስም ጋር የሚመሳሰል እስካልሆነ ድረስ የጥብቅና አገልግሎን ለተወሰነ ስም ፊደላት ወይም ሌላ የሙያ ስያሜ ማስተዋወቅ ይችላል፡፡
. ከአንድ ክልል በላይ ወይም በተለይ የሥልጣን እርከን ደረጃዎች አገልግሎት የሚሰጥ የጥብቅና ድርጅት በሚሠራባቸው ሥፍራዎች እራሱን በአንድ ስም ማስተዋወቅ ይችላል በእያንዳንዱ ክልል እንዲሠራ የተፈቀደለትን የሥልጣን እርከን መግለጽ አለበት
. የጥብቅና ድርጅት አባል የነበረ ጠበቃ በመንግሥት ኃላፊነት ላይ ሲሆን የዚህን ሰው ስም በድረጅቱ መጠሪያነት መገልገል ወይም በድርጅቱ አባላት አንዱ የነበረ መሆኑን መግለጽ የተከለከለ ነው፡፡

፶፭. የሙያ ባልደረባን ስለማክበር
. ማንኛውም ጠበቃ ከሌሎች የሙያ ባልደረቦቹ ጋር የሚኖረው ግንኙነት በቅን ልቦና በመከባበርና በመግባባት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ አለበት
. በፍትህ መድረክ የሙያ ባልደረባን መዝለፍ ማንቋሸሽ ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ ክብሩን ለመቀነስ መሞከር የተከለከለ ነው፡፡
. ማንኛውም ጠበቃ ከደንበኛው ወይም ከሌላ ጠበቃ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ለመቅረጽ የሚፈልግ መሆኑን አስቀድሞ ሳያሳውቅ መቅረጽ የለበትም
. ማንኛውም ጠበቃ ከሙያ ባልደረባው ለሚደርሱት የሥራ ግንኙነት ደብዳቤዎች ተገቢውን ምላሽ የመስጠትና ይህን ግንኙነት አስመለክቶ የተደረገውን ስምምነት የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
. የተለየ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር አንድ ጠበቃ የተከራካሪው ወገን ጠበቃ ሳያውቀው ወይም እርሱ በሌለበት ከተከራካሪው ጋር መደራደር የለበትም፡፡

፶ጜ. በክርክር ወቅት የጠበቃ ግዴታዎች
ማንኛውም ጠበቃ በክርክር ወቅት የሚከተሉትን ድርጊቶች ከመፈጸም መቆጠብ አለበት፡፡
. በምቀኝነት ወይም በክፉ ልቦና ተነሳስቶ ሌላውን ወገን የሚጎዳ ክስ ወይም ክርክር ማቅረብ
.ደንበኛው የወራዳነት ወይም የማጭበርበር ድርጊት እንዲፈጽም ማበረታታት ወይም መፍቀድ
. ዳኛን ወይም ሌላ የፍርድ ቤት ሠራተኛን በሕግ መሠረት ከማሳመን ውጭ ሌላ ተገቢ ያልሆነ ማንኛውም ዓይነት ዘዴ በመጠቀም ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር ወይም በሌላ ሰው እንዲሞክር ማድረግ
.ሆን ብሎ ፍርድ ቤትን የሚያሳስት ወይም የተጋነነ ጽሑፎችና ንግግር ማድረግ
. በምስክርነት ቃል ወይም የሠነድ ይዘት ላይ የሐሰት ድርጊት በመፈጸም ፍርድ ቤት ለማሳሳት መሞከር
.በግልጽ ለጉዳዩ አግባብነት የሌለውን ማስረጃ አግባብነት ያለው አስመስሎ ለፍርድ ቤት ማቅረብ
.ለጉዳዩ በምስክርነት መቅረብ የሚገባው ሰው ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ መቅረብ የሚገባው ሰው ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ማባበል ወይም መምከር
.አንድን ምስክር ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማመናጨቅ ማስጨነቅ ወይም ማስፈራራት

፶፯. አስነዋሪ ከሆኑ ሥነ ምግባሮች ስለመራቅ
ማንኛውም ጠበቃ በሕይወቱ ውስጥ የሙያውን ክብር ሊያጎድፍ ከሚችል ማንኛውም ዓይነት አስነዋሪ ባህሪ የራቀ መሆን አለበት፡፡

፶፰. የሥነ ምግባር ጉድለት መፈጸሙን ስለማሳወቅ
ማንኛውም ጠበቃ ከዚህ በታች የተመለከቱት መፈጸማቸውን እንዳወቀ ድርጊቱን የፈጸመውን ሰው ስምና የጥፋቱን ዓይነት በመግለጽ ለፈቃድ ሰጪው አካል ወይም በአካባቢው ለሚገኘው የፍትሕ አስተዳደር ባለሥልጣን የማስታወቅ ግዴታ አለበት፡
. አንድ ጠበቃ ይህን ደንብ ጥሶ ከተገኘ
.አንድ ሰው የጥብቅና ፈቃድ ሳይኖረው የጥብቅና አገልግሎት ሲሰጥ ከተገኘ ወይም
. አንድ ጠበቃ በጥብቅና ፈቃዱ ከተፈቀደለት ውጭ ሲሠራ ከተገኘ

፶፱. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ መስከረም ፲፫ ቀን ፲፱፻፺፪ .
መለስ ዜናዊ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

 

No comments:

Post a Comment